ዓርብ 29 ሴፕቴምበር 2017

የምሥራቅ ጎጃም ምእመናን VS ቤተክህነት ክፍል 2


ዛሬ መስከረም 19/2010 ዓ.ም ነው፡፡
ነሐሴ 25/2009 ዓ.ም የተካሄደውን የምእመናን እና የካህናት የውይይት መድረክ ነው እየጻፍን ያለነው፡፡
በቤተ-ክህነቱ በኩል የተሰጡ መልሶች
1.     የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የሚገኘው የቆጋ ኪዳነ ምህረት ገዳም አሳታሚነት የታተሙት መጻሕፍት የታተሙ በአቡነ ዘካርያስ ዘመን እንጅ በአቡነ ማርቆስ ዘመን አይደለም የሚል አሳፋሪ መልስ ሰጥተዋል፡፡ ይህን አሳፋሪ መልስ የሰጠው ደግሞ ባህረ ጥበብ የተባለው የሀገረ ስብከቱ ትምህርት ክፍል መምሪያ ኃላፊና ባለ ብዙ ወንበሩና ባለ ሦስት ደመወዙ ሰው ነው፡፡  ማብራሪያ ሲሰጥ ደግሞ ምንም እንኳ መጻሕፍቱ በአቡነ ማርቆስ ዘመን ባይጻፉም ሁለቱን መጻሕፍት የሚሸጡትን ሁለቱን ገዳማት ምስካበ ቅዱሳን ቆጋንና በደ/ማርቆስ ወረዳ ቤተ-ክህነት ስር የሚገኘውን አባ አስራት ገዳም ከዚህ ስራቸው እንዲቆጠቡ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጽፈናል የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡
እዚህ ላይ እስኪ ማብራሪያ እንጨምርበት፡፡



1ኛ. ሁለቱም መጻሕፍት የተጻፉ በተከታታይ ዓመታት ሲሆን ለሽያጭ የወጡትም በተከታታይ ዓመታት ነበር ፡፡ በ2008ና 2009 ዓ.ም ማለት ነው፡፡ የሁለቱ መጻሕፍት ስም በ2008 ለሽያጭ የቀረበው ወልደ አብና በ2009 ዓ.ም ታትሞ በ2009 ለሽያጭ የቀረበ ሚሥጢረ  ሃይማኖት ወትንቢተ ዘዝክሪ ወጳውሊ የሚል ነው ፡፡ ለእነዚህ መጻሕፍት መታተም የአቡነ ማርቆስ እጅ አለበት ብለንም እናምናለን፡፡ ለምን ቢባል መጀመሪያ እነዚህ መጻሕፍት እንዲወገዙ ፊርማ አሰባስበው የጠየቁ የሀገረ ስብከቱ ምእመናን እንደነበሩ እናውቃለን፡፡ እነዚህ ፊርማ አሰባስበው የጠየቁት ምእመናን ወረዳ ቤተክህነቱንም ሀገረ ስብከቱንም የጠየቁ ሲሆን ምንም ዓይነት ምላሽ አልሰጡም ነበር ያ ማለት አባ ማርቆስ ራሳቸው እጃቸው እንዳለበት ያሳያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም  አቡኑ በግንቦት 19/2009 ዓ.ም  ጉንደወይን ከተማ ለቤተ-ክርስቲያን ምርቃት በተገኙበት  ወቅት እነዚህን መጻሕፍት ያሳተመችውን ገዳም ሲያሞካሹ ነበር፡፡ በተጨማሪም ራሳቸው የቀጠሩት መምህር ተብየ ዘላለም ተመስገን ይህን መጽሐፍ በብዛት በደብረ ማርቆስ ከተማ ሳይቀር በማሰራጨት ላይ መሆኑን እያወቁ ዝም ማለታቸው ራሳቸውም እንዳሉበት ያረጋግጣል፡፡
2ኛ.  በየትኛውም ዘመን ይጻፍ አንድ የሃይማኖት አባት ስራው ምንሆነና ነው  በእኔ ዘመን አልተጻፈም በማለት የክህደት መጻሕፍቱን ሲሰራጩ የሚያበረታታ፡፡ በእርግጥ አቡኑም ሆኑ ተከታዮቻቸው ገንዘብ እንጅ ሃይማኖት ጉዳያቸው አለመሆኑን በደንብ አድርጎ ያሳብቅባቸዋል:፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ይህ ስብሰባ በተካሄደ በሁለተኛው ቀን በ27/12/2009 ዓ.ም የቀድሞው የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ የአሁኑ የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዘካርያስ ወልደ አብን አውግዘዋል ፡፡ የውግዘቱን ደብዳቤ ከታች በፎቶው ተመልከቱት ፡፡ ነገር ግን በእርሳቸው ዘመን ተጻፈ የተባለው መጽሐፍስ በእርሳቸው ተወገዘ በ2009 ዓ.ም በአቡነ ማርቆስ ዘመን የተፃፈውን መጽሐፍስ  ማን ያውግዘው የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት፡፡
ለማንኛውም አቡነ ዘካርያስ በእርሳቸው ዘመን የተጻፈውን መጽሕፍ መድረኩ በተካሄደ በሁለተኛው ቀን ያወገዙበትን ደብዳቤ  በመረጃ መረቦች ተለቅቆ ለማየት ለማየት ችለናል ፡፡ ነገር ግን እንደ አባት እርሳቸውስ ቢሆን ለምን ወልደ አብን ብቻ ያወግዛሉ ሚሥጢረሃይማኖት ወትንቢተ ዘዝክሪ ወጳውሊስ ለማን ሊተውት ነው ምን አልባት ሁለት ምክንያቶች ሊኖሩት ይችሉ ይሆናል ብለን እናስባለን፡፡
1ኛ. አቡነ ዘካርያስ ራሳቸውን ነጻ ለማድረግ ብቻ የጻፉት እንጅ አምነውበት ለምእመናን አስበው ያደረጉት እንዳልሆነ ያሳያል፡፡ እርሳቸው ይህን መጽሐፍ ያወገዙት ስብሰባው ነሐሴ 25 ተደርጎ ነሐሴ 27 ከሁለት ቀናት ቆይታ በኋላ መሆኑ ምናልባትም ከተሰበሰቡት ካህናት መካከል ለአቡነ ዘካርያስ መረጃ ያቀበለ ሰው እንዳለ ያሳያል፡፡
2ኛ. ከሚኖሩበት ሀገር መጽሀፉ አልደረሰም ፡፡ ምናልባትም በርካታ የተዋሕዶ ልጆች ይህን መጽሐፍ በተመለከተ በማኅበራዊ ሚዲያዎች መልስ ይሰጡበት ስለ፤ነበር ይህንን አይተው ሊሆን እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በ2009 ዓ.ም የርክበ ካህናቱ ሲኖዶስ አገር ቤት ገብተው ስለነበር የመጽሐፉንም ጉዳይ አይተውት ሊሆን ይችላል፡፡

2.    የዘመደ አዝማድ ጉዳይን በተመለከተ አንዳንዶች ሲመልሱ እኔ ለምሳሌ ምሥራቅ ጎጃም አይደለሁም ተፈትኜ በውጤቴ የተቀጠርኩ ነኝ የሚል ገራሚና አሳፋሪ መልስ ሰጥተዋል፡፡ ደፍረው ግን ሊመልሱት ያልቻሉት ነው፡፡ ሀገረ ስብከቱ የአቡነ ማርቆስ የሥጋ ዘመዶች የተሰባሰቡበት እንደሆነ ለማንም የታወቀ ነው፡፡ ምናልባትም ዘመድ ያልሆኑ ጥቂት ሠራተኞች ቢገኙ እንኳ ማኅበረ ቅዱሳንን ለመዝጋት አልያም ሰንበት ትምህርት ቤቶችን ለማዳከም ተልእኮውን በብቃት እንወጣለን ብለው ጉቦ የከፈሉ እንደሚሆኑ ለማንም የታወቀ ነው፡፡
3.    የገዳመ አስቄጥስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም የሒሳብ ፈራሚዎችን በተመለከተ ከዚህ ቀደም የገንዘብ ብዝበዛ ስለነበር እርሱን ለማስቀረት ነው የሚሉ መልሶችን ሰጥተዋል፡፡ በእውነት ግን አንድ ሊቀ ጳጳስ ለአንድ ገዳም ገንዘብ አንቀሳቃሽ ሊሆኑ የሚችሉበት ህግ አለ ወይ ይህ በጥልቀት መታየት አለበት፡፡ ከዚህ በፊት ገንዘብ መዝብረዋል የተባሉ ግለሰቦች ካሉስ ለምን በሕግ አይጠየቁም ነበር ግን ውሸት ነዋ፡፡
4.    የብድሩ ሁኔታ አልጠየቅንም ፡፡ ተመላሽ የሆነው ብርም የሀገረ ስብከቱ ድርሻ ብቻ ነው፡፡ የሞጣ ወረዳ ቤተ-ክህነት የሚባለውን ነገር ግን እኔም የሰማሁ እዚሁ ነው የሚል ምላሽ በሀገረ ስብከቱ ስራአስኪያጅ በአባ እንባቆም ጫኔ ቀርቧል፡፡
የተቀመጡ መፍትሔዎች
1.     የመጀመሪያው መፍትሔ ጉዳዩ አስተዳደራዊው ጉዳይም መሰረቱ ሃይማኖታዊ ስለሆነ የሲኖዶስን ውሳኔ መጠበቅ አለበት ተብሏል፡፡ ይህ ተፈጽሟል አልተፈጸመም ገምግሙት፡፡
2.    በዕለታዊ አስተዳደር ችግር አለመፍጠር ተብሏል፡፡ ይህ ተፈጽሟል አልተፈጸመም ገምግሙት፡፡

3.    ቅኔ ለበስ የሆነው የስብከት አሰጣጥ ይቁም፡፡ ሠላም የሚያመጣ ስብከት ይሰበክ ተብሏል፡፡ ይህ ተፈጽሟል አልተፈጸመም ገምግሙት፡፡

4.    ለቀብር ማስፈጸሚያ የሚጠየቀው የገንዘብ ክፍያ ይቁም ተብሏል፡፡ ይህ ተፈጽሟል አልተፈጸመም ገምግሙት፡፡

5.    የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔን እናክብር ተብሏል፡፡ ይህ ተፈጽሟል አልተፈጸመም ገምግሙት፡፡
6.   ሰ/ት/ቤቶችና ማኅበረ ቅዱሳን በመተዳደሪያ ደንባቸው መሰረት ከዚህ ቀደም በመጡበት አግባብ አገልግሎታቸውን ያስቀጥሉ ፡፡ የተዘጉ ሰ/ት/ቤቶች እንዲከፈቱ ተብሏል ይህ ተፈጽሟል አልተፈጸመም ገምግሙት፡፡
7.    አብዛኞቻችሁ የችግሩ ፈጣሪ መነኮሳት ናችሁ፡፡ ምንድን ነው የምትፈልጉት? ሰ/ት/ቤትና ማኅበረ ቅዱሳንን ለምንድን ነው የምትጠሉት? ስለተማሩ ችግራችሁን በደንብ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ አይደለም እንዴ ስለዚህ አቅርቧቸው ጥያቄ መጠየቅም መብታቸው ነው፡፡ ቦታው የገበያ ቦታ አይደለም፡፡ ቤተ-ክርስቲያን የህዝብ ናት ህዝብ ያስተዳድራት፡፡ በሰበካ ጉባኤ በአባት አደሯ ትመራ ተብሏል፡፡ ይህ ተፈጽሟል አልተፈጸመም ገምግሙት፡፡
8.    ከፌስ ቡክ ፕሪንት አድርጎ የሚያስተምር ምን ዓይነት አባት ነው ፡፡ ስለዚህ መድረኩ የእነርሱ ብቻ ስለሆነ እንደፈለገ ባያደርጉት፡፡ለመሆኑ ቤተ-ክርስቲያን የማን ናት፡፡ ፌስቡክ ላይ እገሌ የሚባል ሰው እንዲህ ብሎ ጽፏል እያሉ በየመድረኩ ማንሣታቸው ተገቢ አለመሆኑን ተጠቁመዋል፡፡ በተለይም ከቅባት እና ተዋሕዶ ጋራ በተያያዘ ጉዳይ ላይ የሚጻፉትን ጽሑፎች ከፌስቡክ ላይ ፕሪንት አድርገው ማቅረብ ተገቢ አለመሆኑ ተነግሯል፡፡ ይህ ተፈጽሟል አልተፈጸመም ገምግሙት፡፡
9.   አንደ ከብት ከበረት ውስጥ የምትበጠብጥ ከሆነ እርሷን ከበረቱ አውጥቶ መጣል የተሻለ ነው ፡፡ የሚደረገውም ይኼው ነበር፡፡ ስለዚህ ከስረ መሰረቱ በጥባጭ ከበረታችን ይውጣልን ተብሏል፡፡ ይህ ተፈጽሟል አልተፈጸመም ገምግሙት፡፡
10.   ሰበካ ጉባኤ የሌላቸው አጥቢያ አብያተ-ክርስቲያናት ከሁሉም ተወካዮች ቃለ አዋዲው በሚያዝዘው መሰረት ይቋቋሙ የሚል መፍትሄ የተቀመጡ ሲሆን በማጠቃለያ ወደ መንግስት አመራሮች የመጣ ሲሆን የሚከተሉትን አስተያየትና የማጠቃለያ ሀሳብ ሰጥተዋል
በመጨረሻ የመንግስት አካላት ሀሳባቸውንና መፍትሄ የሚሉትን አስቀምጠዋል
1.    የዞኑ አስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ የሰጡት አስተያየት
o   ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ሁሉም አለ ፡፡ያውም የእምነት ጉዳይ በመሆኑ ጉዳዩን ሁሉም  የተቀላቀለው ነው ብለዋል፡፡
o   መነሻ ነጥቡ ምንድን ነው ብለን ስናጠና እንደኛ ተቋም በሦሰት ዓይተነዋል(አስተዳደራዊ ጉዳዩን ብቻ) ብለው ዘርዝረዋል፡፡
1ኛ. የመልካም አስተዳደር ችግር
-      ቤተክህነቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ የአሰራር ብልሹነት እና ችግር አለ
-      ውስጣቸው ላይ ችግሩን ለመፍታት ቁርጠኝነት የላቸውም
-      ቅጥር አፈጻጸሙም ቢሆን ቤተሰብን የማሰለፍ ጉዳይ ስላልሆነ ትኩረት መሰጠት አለበት
-      ያለአግባብ የሚባረሩ አሉ ግትር ያለ አቋም ነው ያላቸው
-      በአጠቃላይ ውስጡ ላይ የመልካም አስተዳደር ችግር ስላላ ሲበጠበጥ መኖሩ አይቀርም
                             I.        የጥቅም ግጭት አለ
                            II.        የመናናቅ ችግር አለ
-      መከባበር የለም
-      መከባበር የሚባለው ጉዳይ የሚጠፋው ደግሞ የአመራር ችግር ስላለ ነው
ታዲያ እኛ ከእናንተ ምን እንማር ???
እንደ መፍትሔ የተቀመጡትም ነጥቦች፡
o  አሰራሩ መከበር አለበት(ቃለ አዋዲ፣ የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብና የሰ/ት/ቤት መተዳደሪያ ደንብ ) እንዲከበር ጭምር አብረን እንሰራለን፡፡
-      አሰራሩን ከተከተልን መከባባር የሚባለው ነገር ይመጣል፡፡
-       አንድ አባት የማይከበረው አሰራሩን ካልተከተለ ብቻ ነው
-      በሃይማኖት አባቶችም በኩል ሁለት ቡድን አለ
-      የአሰራር ጥሰት ካለ እኛ እንደ መንግስት ቁጥጥር እናደርጋለን
-      ችግሮችን የምንፈታበት ሂደት ከሌለ ችግሮችን ለመፍታት በኃይል የሚሄድበት ጉዳይ ይመጣል
-      ሃይማኖታዊ የሆነውን ጉዳይ በውስጣቸው ይፍቱ በሚል ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በመቀጠልም የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ዶ.ር ንጉሤ ምትኩ እንዲህ ብለዋል፡፡
/ር ንጉሴ የደ/ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት ያቀረቡት ሃሳብ፡፡
v የተቋቋምንለትን ዓላማ ምንድን ነው ብለን ከተነሳን ጥል የለም የሚል ትልቅ አባባል ተናግረዋል፡፡
v የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ታሪክ ተጠብቆ እንዲቆይ ለማድረግ በቁርጠኝነት መነሳት የማይፈልግ ካለ እርሱ በደንብ መታየት አለበት ብለዋል፡፡
v አይደለም ሳንግባባ ተግባብተንም ይህን እምነት የድሮውን አቋም/ቁመና ይዞ እንዲቀጥል ማድረግ ከባድ ነው በዚህ geo political ሁኔታ ውስጥ ስላለን፡፡
v የተቀመጡት መፍትሔዎች ጥሩ ናቸው፡፡ ግን እጠራጠራለሁ በተለይ የእድማጣውን አስተዳደሪና ሰበካ ጉባኤ ለምን በእኔ ተቋም እንኳ ጉዳዩን ለመፍታት ስንት ግዜ ጥረት አድርገናል፡፡እውነቱን እውነት ማለት ግድ ይላል፡፡
v ግቢ ጉባኤ የሚማሩት ሃይማኖት ብቻ አይደለም ስነ-ምግባርም ጭምር እንጅ አንዱ የስነ-ዜጋ ትምህርት የሚማሩበት ትምህርት ቤት ነው ግቢ ጉባዔ፡፡
v መምከር ማስተማር ጥሩ ነው ፡፡ የመንግስት አካል የሚያስታርቃችሁ ከሆነ የምትመሩት ምእመን  ነገ ይጠላችኋል፡፡ የእኔ እምነት ተሸርሽሯል ብለዋል፡፡
v የቤተ-ክህነት ሰው በእምነት ከተጠረጠረ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ ቤተ-ክርስቲያን የህዝብ ናት፡፡ ቅጥርም ከገንዘብ እና ከዝምድና ጋር የተያያዘ መሆን የለበትም፡፡
v የነበሩ አሰራሮች ይቀጥሉ፡፡ ሰ/ት/ቤትና ማኅበረ ቅዱሳንም አካባቢ የእምነት አባቶች ናቸውና እናክብራቸው አክብሯቸውም ብለዋል፡፡
v ማኅበረ ቅዱሳን እንደ ደጋፊ አካል ቁጠሩት ሰ/ት/ቤትንም እንደዚያው፡፡
v ግቢ ጉባኤን በተመለከተ ገንዘብ ስጡን ለማለትና ገንዘብ ለመሰብሰብ መግባባት ያስፈልጋል፡፡ እንደ ልጅ እንያቸው ፡፡ ከኪሳቸው የሰበሰቡትን ብር ያለመስጠት መብት አላቸው፡፡ በእኔ ኪስ ማንም አያዝዝምና ብለዋል፡፡
ከዚህ በኋላ የከተማው ከንቲባ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡
በደ/ማርቆስ ከተማ ከንቲባ በኩል የተነሡ ሃሳቦች
o   ዓላማችንን እንመልከት የሚለውን የዶ/ር ንጉሴን ሀሳብ እንያዝ ብለዋል፡፡
o   የአሰራር ግልፀኝነት ይኑር፡፡የራሷን ችግር ራሷ ትፍታም ብለዋል፡፡
o   ሌሎች አህጉረ ስብከቶች ላይ የማኅበረ ቅዱሳን መዋቅርም ሰ/ት/ቤትም አለ ፡፡ ሲጣሉ ሰምተን አናውቅም አስፈላጊም ከሆነ መተዳደሪያ ደንቦችን እንዴት እንደሚተረጉሙት ልምድ ልውውጥ የሚያካፍል ሰው እናምጣ ብለዋል፡፡
o   ምንም ዓይነት ልጅ የላችሁ ፍቅረ ንዋይ ግን አጥቅቷችኋል ብለዋል፡፡
o   የተጓደሉ ኮሚቴዎች ቶሎ ይቋቋሙ እና ሥራ ይጀምሩ ብለዋል፡፡
o   የሠላም ኮሚቴ በአስተዳዳሪው ቢቋቋም የሚል ሃሳብም አምጥተዋል፡፡
ከዚህ በኋላ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አማካሪ ሃሳባቸውን አቅርበዋል፡፡
በዋና አስተዳዳሪው አማካሪ የተነሡ ሃሳቦች፡፡
·       ችግሮች ለእኛ የሚመጥኑ አይደሉም፡፡ ብዙ ችግር ቀዳችሁ መስፋት የምትችሉ ሰዎች እያላችሁ እንዴት ይህ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡
·       አንድ ሰው ለሁለት አምላክ አይገዛም ብላችሁ ያስተማራችሁን እናንተ ናችሁ አማረ ከእናንተ ሰምቶ እንደተናገረው የገንዘብ ፍቅር ይዟችኋል ፡፡ ለሃይማኖት እደሩ ብለዋል፡፡
·       እንድማጣ አካባቢ ለማስተማር ሳይሆን በማስተማር የሚገኝ ጥቅም ካለ በሚል የምታነሱት ጉዳይ ነው፡፡ ይህማ ከሆነ ነገ ደግሞ አዲስ የምንገነባው ዩኒቨርስቲ አለ አቡነ ገ/መንፈስ ቅዱስም ያሉ ሰዎች የእርስ መካፈል አይነት ጉዳይ ነው የሚሆነው ፡፡ ይኼ ሊቆም ግድ ይላል፡፡ደ/ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ባይመጣ ኖሮ ምን ሊሰራው ነበር ፡፡ በግለሰብ ብር አትጣሉ ብሏ፡፡
·       እውነት ክርስቶስ ይህንን አስተምሯል፡፡ ዝቅ ብሎ ከዝቅተኛ ሰው ጋር የሚነጋገር የሚስተምር አባት ቢኖር ኖሮ ይህ ጉዳይ አይመጣም ነበር ፡፡
·       የምሁራን ፍልሰት እንዳይመጣ እንጠንቀቅ ብለዋል፡፡
በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ የተነሡ ሃሳቦች
v አጠቃላይ ውይይቱ በጣም ጥሩ ነበር፡፡
v ውይይቱ የመፍትሄው አንዱ እርምጃ ነው ፡፡ህዝቡ ጤነኛ ነው ፤ህዝቡ ጤና ነው በዚህ ከቀጠለ ሊታመም ይችላል፡፡ ከተቆጣም የመጀመሪያ ጥቃት የሚያደርሰው ከእናንተ ከመሪዎች ላይ ነው፡፡
v አካባቢው ብዙ ምሁራንን ያወጣ ነው፡፡
v ልማት ያለዚች ቤተ-ክርስቲያን አይታሰብም በተለይ ለዚህ ዞን ምክንያቱም 97 ፐርሰንት በላይ የዚህ እምነት ተከታይ ስለሆነ ብለዋል፡፡
v አባትነት ሲደረስ ብዙ ኃላፊነት አለው፡፡ እዚህ ተምሬ ይህንን ተምሬ  ሀሳባችሁ ነው ብየ ነው እንጅ የወረደ ነው፡፡ መሬት ላይ የምንጠይቃችሁ አይመስለኝም ግን ደግሞ እንደዚህ ብታስተዳድሩን ብሎ መጠየቅ ኃጢአት አይደለም፡፡ደንገጥ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ማሸግ /ማባረር ለእኔ የወረደ እርምጃ ነው ፡፡ትንሹን ነገር ወደ ጫካ አንውሰደው፡፡
-      በተማሪ ገንዘብ መጣላት ለእኔ አሳፋሪ ነው ፡፡ሰው የሚሰማው ጉዳይ አይመስለኝም፡፡ አሳፋሪ ነው የልጅነትና የአባትነት ሚዛን የሚያጠፋ ነው ብለዋል፡፡

ይህንን ሃሳብ ይዤ ምእመናንንም ለማነጋገር ሞክሬ ነበር፡፡ የተሰበሰቡት ምእመናን ተወካዮች የሚከተለውን ሃሳብ ሰንዝረዋል፡፡
1.     አባቶች መከበር አለባቸው በሚለው ሃሳብ እንደሚስማሙ ገልጸው፡፡
-      ሃይማኖታዊ ጉዳይ መጠየቅ ግን ይቻላል መብታችን ስለሆነ ብለዋል፡፡
-      በዝምድና መቅጠር ለእኛ እጅግ አሳፋሪ ነው በእውነትም እናፍራለን፡፡ በስም እገሌ እገሌ ተብሎ እስኪጠቀሱ ድረስ እኮ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ መረጃ መስጠት የሚፈልጉ አባቶች ስማቸው እንዳይገለጥባቸው ያስጠነቅቃሉ ይህ ማለት በአቡነ ማርቆስ በኩል ከፍተገኛ ተጽእኖ ይደርስባቸዋል ማለት ነው፡፡
2.    ህግ ይከበር(ቃለ አዋዲ፣ የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብና የሰ/ት/ቤት መተዳደሪያ ደንብ) የሚለውን እንቀበለዋለን፡፡
3.    በእኛ በምእመናን በኩል ክፍተት ካለብን እንጠየቅ፡፡ እንደ አባትነታቸው ምከሩን ይገስጹን፡፡ በማለት ገልጸውልናል፡፡
በመጨረሻም የጉባዔው አጠቃላይ ሃሳብ ተተቃሎ ቀርቧል፡፡ በዚህም መሠረት እንደሚከተለው ማጠቃለያ ሃሳብ ተሰጥቷል፡፡
-      የመንግሥት አካል እንዲህ በሏል፡፡ እኛ ሰውን ማሰር አንፈልግም ሆስፒታል እንሰራበታለን፡፡ ግን ወደዚያ የሚያመራ ጉዳይ ካለ በሁለቱም ወገን ሰው የማሰሩን ጉዳይ ተገደን እናደርገዋለን፡፡ እኛም የምንሰሳትበት የሚያሳስተን ጉዳይ ሆኖ ይመጣል፡፡

-      ለጥያቄ በር መዝጋት መፍትሔ አይደለም ፡፡ አንድ ሰው የሆነ ነገር ላይ ደርሻለሁ ካለ ያ ሰው ብቻ አይደለም ብዙ ሰው ላይ ደርሷል፡፡

-      የነበሩ አሰራሮች በነበሩበት ይቀጥሉ፡፡ ሰበካ ጉባኤ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ቶሎ ብለው ይስተካከሉ፡፡ በአንድ ሳምንት ውስጥ ተብሎ ተወስኖ ነበር የመጣ ለውጥ ስለመኖር አለመኖሩ ባይታወቅም፡፡

-      በወሩ ደግሞ ሌላ የአንድ ቀን ግምገማ (በመጡ ለውጦች) ውይይት እንዲኖር እናደርጋለን  ተብሎ ነበር በዚህም መሰረት በዚህ ወር ስብሰባ ሊኖር እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን፡፡

-      በመጨረሻ የሠላም ኮሚቴ እንዲቋቋም ጉዳዩን ለአስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊነት ተሰጥቶ ጉዳዩ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሲሆን ተጠናቅቋል፡፡
ማስታዋሻ፡-
-      የመንግስት አመራሮች ለጉዳዩ የሰጡት ትኩረት በጣም ጥሩ እንደነበር መረዳት ችለናል፡፡
-      ጉዳዩን ገለልተኛ በሆነ መልኩ  ለመምራት የሚያደርጉት ጥረት የሚያስመሰግናቸው ጉዳይ እንደሆነ ሆኖ ለውጦችን በመከታተል በኩል ግን ቀጣይ የቤት ስራ እንደሚሆን እየገመትን ቤተ-ክህነቱ ግን የፊውዳል አመራር ያላቸው በመሆኑ ለውጡ ስለመምጣቱ እየተጠራጠርን ለውጡ እንዳይመጣ በሚያደርጉ ግለሰቦች ላይ ግን ህጋዊ እርምጃ እስካልተወሰደ ድረስ ምንም ዓይነት ለውጥ ይመጣል የሚል ግምት የለንም፡፡ ለምን ባለፉት የአቡነ ማርቆስ የግዛት ዘመን የተረዳነው ጉዳይ ያለ በመሆኑ ነው፡፡
-      ግን የመጣ ምንም ዓይነት ለውጥ እስከ አሁን አልታየም ፡፡
በቀጣይም መረጃዎችን እየሰበሰብኩ አቀርብላችኋለሁ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

አባ ወልደ ትንሣኤ ባንቲገኝ VS መልእልተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ ሰ/ት/ቤት

ዛሬ ጥቅምት 5/2010 ኣ.ም ነው፡፡ ============================= ·          ጸለተ ምሕላው እንደቀጠለ ነው፡፡ ·          ጽጌን በቤተክርስቲያን እያደርን በረከተ ሥጋ ወነ...