ዓርብ 28 ጁላይ 2017

ሰሙነ ሕማማት ----ጦማር አንድ


========================================

ይህ ሳምንት ከሰርከ ሆሳዕና እስከ ትንሣኤ ያሉትን ቀናት ያካትታል:: የጌታን መከራ እንግልት መሰቀል መሞት መቀበር የምናስብበት ነው:: ለእኛ ሲል የተቀበላቸውን 13 ሕማማተ መስቀል በማሰብ በልቅሶ በስግደት በጸሎት ልናሳልፈው ይገባል:: በዚህ ሳምንት ሊሰሩ ያልተፈቀዱ በርካታ ናቸው:: በመስቀል መባረክ ማማተብ መሳቅ መሳሳም ከሴት ጋር መገናኘት ኑዛዜ መፈጸም ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን 5500 የጨለማ ዘመን መታሰቢያ በመሆኑ መንበሩ በጥቁር ልብስ ይሸፈናል ካሕናትም ጥቁር ይለብሳሉ:: በዚህ ሳምንት ለሞተ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይለትም ክርስትናም እንዲሁ አይፈጸምም:: እግዚአብሔር ይፍታህ አይባልም ሳምንቱ የሚታሰበው ሕማሙን ሞቱን በማሰብና በስግደት ነው:: የግዝት በዓላት እንኳ ይሰገድባቸዋል:: የዚህ ሳምንት ጾም የቻለ ሁለት ሁለት ቀን ያልቻለ እስከ ጀንበር ግባት ድረስ ነው:: ምግቡም ቆሎ ዳቦ የላመ የጣመ ያልሆነ ደረቁን በበርበሬ ነው መጠጡም ንጹህ ውኃ ነው:: ጠጅ ያንቆረቆረ ጮማ የቆረጠ እድል ፈንታው ጽዋእ ተርታው በጌታ ሞት ከተደሰቱት ከአይሁድ ጋር ነው:: ጸሎቱ ውዳሴማ ርያም አንቀጸ ብርሃን መልክአ ሕማማት መዝሙረ ዳዊት ነው:: የቅዱሳን መልክአ መልክእ አይጸለይም::  የጾሙ ሥርዓት ምን ይመስላል ካሉ፡

አባ ወልደ ትንሣኤ ባንቲገኝ VS መልእልተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ ሰ/ት/ቤት

ዛሬ ጥቅምት 5/2010 ኣ.ም ነው፡፡ ============================= ·          ጸለተ ምሕላው እንደቀጠለ ነው፡፡ ·          ጽጌን በቤተክርስቲያን እያደርን በረከተ ሥጋ ወነ...