እሑድ 15 ኦክቶበር 2017

አባ ወልደ ትንሣኤ ባንቲገኝ VS መልእልተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ ሰ/ት/ቤት


ዛሬ ጥቅምት 5/2010 ኣ.ም ነው፡፡
=============================
·         ጸለተ ምሕላው እንደቀጠለ ነው፡፡
·         ጽጌን በቤተክርስቲያን እያደርን በረከተ ሥጋ ወነፍስን እንሸምትበት፡፡
·         ሲኖዶሱ እሁድ ጥቅምት 12/2010 ዓ.ም በጸሎት ይከፍታል፡፡
·         በየወረዳው አቡነ ማርቆስን እንዲነሡልን የሚጠይቁ የተዋሕዶ ልጆች ተባራክተዋል፡፡
·         በተሐድሶዎቹ ላይ የተያዘው አቋም እንዲበረታታ ቅዱስ ሲኖዶስን የሚጠይቅ የህዝብ ፊርማ እየተሰባሰበ ነው፡፡
·         ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን ቅዱስ ሲኖዶስን በይፋ ይቅርታ ጠይቀች እነ ዳግማዊ ደርቤ እና ሃብታሙ ሽብሩም የምርትነሽን መንገድ እንደሚከተሉ አሳውቀዋል፡፡
·         አባ ወልደ ትንሣኤ ባንቲገኝ የመልእልተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ ሰ/ት/ቤትን ለማዳከም እየሠሩ እንደሆነ መረጃ ደርሶኛል ወደዚሁ እንለፍ፡፡





ይህ መረጃ የተዋሕዶ አርበኛ ከሆኑ ውስጠ ምሥጢሩን ፈትፍተው ከሚያውቁ ልጆች በውስጥ መስመር የደረሰኝ ነው፡፡ ተናግሬ ነበር እባካችሁ በውስጥ መስመር እየገባችሁ ምንም ዓይነት መረጃ ሳይኖራችሁ “Hi” እያላችሁ አታድርቁኝ፡፡ መረጃ የሌላችሁ ሰዎች ውስጥ መስመሩን አታጨናንቁት፡፡ የመረጃ አቀባዮቼን መስመር አታጨናንቁት እሽ፡፡ አልሰማም ካላችሁ #BLOCK ስላለልኝ በቀላሉ ነው የምፋታችሁ እናንተን ለመፋታት የእናንተን ሰማንያ ለመቅደድ ደግሞ ፍርድ ቤት ልሄድላችሁ ነው እንዴ አረ #BLOCK በቀላሉ ያፋታናል፡፡
መረጃየ “እቅዱ ተሳካ አባ ወልደ ትንሣኤ ባንቲገኝ በደብረ ማርቆስ ከተማ ለሚገኘው መልእልተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ አስተዳዳሪ ሆነው በአባ ማርቆስ የተሾሙ ሲሆኑ አንጋፋውን የቅዱስ ማርቆስ ሰንበት ትምህርት ቤቱን አፈራረሱት”  ብሎ ነው የጀመረው፡፡ አባ ወልደትንሣኤ ባንቲገኝ ከአባ ማርቆስ ምን ዓይነት ተልእኮ እንደወሰዱ ከዚህ በፊት በሰፊው አብራርቸላችኋለሁ፡፡ እንዲያም በ16/12/2009 ዓ.ም ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ላይ የቀይ ካርድ የተመዘዘባቸው የመጀመሪያው መነኩሴ ናቸው፡፡  እኒህ አባት ይላሉ የተዋሕዶ አርበኛ የሆኑት የመረጃ ምንጮቼ “ከአቡነ ማርቆስ የተቀበሉት የመጀመሪያው ተልእኮ ይህንን ሰንበት ትምህርት ቤት ማድከም ከቻሉም፣ ማፍረስ ነበር ይህንንም ተግባራቸውን በብቃት እና በታማኝነት ተወጥተው ከአቡነ ማርቆስ የድል አክሊልን ለመቀበል ሌት ከቀን እንቅልፍ በማጣት፤ ላይ ታች እያሉ ሲሉ ኖረው ይኸው እቅዱ ተሳካላቸው” ይላሉ፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤቱን ለማዳከም ያደረጉት ጥረትም በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ከዚህ በፊት እንደገለጽነው የአባ ወልደ ትንሣኤ ሰንበት ትምህርት ቤቱን የማዳከም ሙከራ የጀመረው “የደብረ ማርቆስ ተወላጅ ካልሆናችሁ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት መሆን አትችሉም” በሚለው ውኃ የማይቋጥረው ሃሳባቸው ነበር፡፡ እንደ አባ ወልደ ትንሣኤ ሃሳብ ከሆነ አንድ ወጣት በቃለ ዓዋዲው በተቀመጠለት መመሪያ መሠረት ሳይሆን ተወላጅነቱ የየት አካባቢ ነው የሚለው መጠናት አለበት ባይ ናቸው፡፡ ይህንንም መመሪያ የተቀበሉት ከላይ ከአባ ማርቆስ እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ አባ ማርቆስ ይህንን ሃሳብ የፈበረኩት ከሌላ ቦታ የመጡ ሰዎች ተዋሕዶ ስለሆኑ ቅባቶችን ተጠመቁ ይላሉ ብለው ስላሰቡ ነው፡፡ እንዲያውም ከሌላ ቦታ የሚመጡትን ሰዎች “ሸቃላይ ሌባ” በማለትም ተናግረዋል፡፡ በዚህም መሠረት የምግባር ችግር ያለባቸውን ወጣቶች ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ በማድረግ ሾመዋል፡፡ በነገራችን ላይ ከሌላ አካባቢ የመጣ ሰው ሰንበት ትምህርት ቤት አባል መሆን አትችልም የሚባለው እነ አባወልደ ትንሣኤ ለይተው ከያዟቸው ቦታዎች ከመጣ ብቻ ነው፡፡ ከጉንደወይን ብትመጣ ከደብረ ወርቅ ብትመጣ ከመርጡለማርያም ብትመጣ ከሞጣ ብትመጣ ከረቡዕ ገበያ ብትመጣ ከሉማሜ ብትመጣ ከቢቡኝ ብትመጣ ቅባትነትህ ተጣርቶ ይፈቀድልሃል፡፡ ቅባት ካልሆንህ ግን ከእነዚህ ቦታዎች ብትመጣም የሚሰማህ የለም፡፡ ዋና ተልእኮው ሰንበት ትምህርት ቤቱን ማዳከም ስለሆነ ማዳከም የሚችሉበትን ማንኛውንም መንገድ ሁሉ ይከተላሉ፡፡
የመረጃ ምንጨ ሰንበት ትምህርት ቤቱን ለማዳከም አባ ወልደ ትንሣኤ ባንቲገኝ ያዋቀሩትን አዲስ የሰንበት ትምህርት ቤት ሥራ አስፈጻሚ ከነስልካቸው እንዲህ ይዘረዝራል፡፡ አዲስ የተመሰረተው የቅዱስ ማርቆስ //ቤት መዋቅር
·         1 / በቃሉ ሞላ …………. ሰብሳቢ ስልክ ቁጥር  0983574923  ማብራሪያ ሲሰጡም የረቡዕ ገበያ ተወላጅ ዋና የቅባት አቀንቃኝ አፋቸው የሚሰብከው ተዋሕዶን ነው ልባቸው ግን ቅባት ነው ለቅዱስ ማርቆስ //ቤት መፍረስ ከአስተዳዳሪው ጋር በመሆን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድረገዋል፡፡
·         2ኛ.ሳሙኤል ገበየሁ………….መዝሙር ክፍል  ስልክ ቁጥር 0933555444
·          3. አቤል ገበየሁ…… /ያዥ ስልክ ቁጥር  0920469708 እነዚህ  ሁለቱ መንትያ ወንድማማቾች ናቸው፡፡
·         4ኛ.ፍቅረሥላሴ አበበ …./ሰብሳቢ ስልክ ቁጥር 0910295313 አባቱ አበበ ብርሃኑ ይባላሉ፡፡
·         5ኛ.ማስረሻ ወንድሜነህ….. ፀሐፊ ስልክ ቁጥር  0939619467 የሚኖረው ሆስፒታል ኮንዶሚኒየም አካባቢ ነው፡፡
·         6. ቤተልሄም ተስፋሁን…. አባል  ስልክ ቁጥር 0946976750 ይች ልጅ ደግሞ እናቷ ዘነበች የሚባሉ ናቸው፡፡
አጠቃላይ ስለሆነው ስለነዚህ ማብራሪያ ሲሰጡም እንዲህ ብለዋል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ከሰ//ቤቱ በስነ ምግባር ህፀፅ ተባረው የነበሩ ናቸው እነዚህ ግለሰቦች ከሰንበት ትምህርት ቤቱ መቼ እና እንዴት ተባረሩ ብለን እንጠይቅና መልሱን እንመልስ፡፡ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ልጆች ከሰንበት ትምህርት ቤቱ የተባረሩት በምግባር ህጸጽ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ተመክረዋል ተዘክረዋል ሆኖም ግን 2008 / በጣም አስጸያፊ ተግባር ፈጽመው ስለተገኙ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ በዓለ ትንሣኤ ነው 2008 / የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ደካሞችን ለማግደፍ ከዚያ ዚያ ይሯሯጣሉ፡፡ እነዚህ ከላይ የጻፍናቸው ልጆች ግን ምንም እንኳ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ውስጥ አባል ነን ብለው ቢያወሩም ተግባራቸው ግን ሌላ ነበር፡፡ ደብረ ማርቆስ ከተማ #ሳሚ_ህንጻ_ኦኬ_ባር_ከሚባል_ጭፈራ_ቤት ውስጥ ጥንድ ጥንድ በመሆን ዳንኪራቸውን ይረግጣሉ፡፡ መጠጣቸውንም እንዲሁ እየተቀባበሉ ይጋታሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ጭፈራ ቤቱ ሲዘጋ እነዚህ ጉደኞች ጥንድ ጥንድ እንደሆኑ ተያይዘው ሆስፒታል ኮንዶሚኒየም በረንዳ ላይ ወድቀው ያድራሉ፡፡ እነዚህን ልጆች በዚህ መልኩ ያያቸው ሰው ሁሉ እነዚህ የቅዱስ ማርቆስ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት አይደሉም እንዴ? እያለ ሰንበት ትምህርት ቤቱን መርገም እና መሳደብ ጀመረ፡፡ በዚህ የተነሣ ተከብሮ የኖረውን ታላቁን ሰንበት ትምህርት ቤት በማሰደባቸው ከዚህ በፊትም ተመክረው ተዘክረው ስላልተመለሱ እርምጃ ይወሰድባቸው ዘንድ #ከሀገረ_ስብከቱ_ሥራ_አስኪጅ_አባ_እንባቆም_ጫኔ ላይ ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ ሆኖም ግን አባ እንባቆምም ይህ የሀገረ ስብከቱ ችግር ስላልሆነ ወረዳ ቤተክህነቱ ችግራችሁን ይፍታላችሁ ተባሉ፡፡ ከዚያም የደብረ ማርቆስ ከተማ ወረዳ ቤተክህነት ሥራ አስኪጅ ልዑል እና የከተማው ሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያው ኃላፊ መርጌታ መሠረት በተገኙበት ከፍተኛ ውይይት ተደርጎ እነዚህ ከላይ የዘረዘርናቸው ግለሰቦች የመጨረሻ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ በቃለ ጉባዔ ተይዞ ተሰጣው፡፡ የቃለ ጉባዔውም ግልባጭ ለሀገረ ስብከቱ፣ ለወረዳ ቤተክህነቱ፣ ለደብሩ ሰበካ ጉባዔ፣ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ደርሷል፡፡ ይህ ሁሉ እየታወቀ /ፀሐይ አባ ወልደ ትንሳኤ የመልዕልተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ //ቤት ኮሚቴ አድርገው በድጋሜ ሾሟቸው የሹመቱን ደብዳቤ ወደፊት እናቀርባለን፡፡ በማለት መረጃዎችን ወደፊት እንደሚልኩ ገልጸው ሃሳባቸውን ይቀጥላሉ፡፡ በነገራችን ላይ ይህንን መረጃ በራሴ ገጽ ለቅቄውም ነበር ነገር ግን በቅርብ መረጃ ያልተጠናከረ ስለነበረ አሁን በቂ ማስረጃዎችን ዋቢ አድርገን ነው የጻፍነው፡፡ መረጃ ምንጨ አሁንም እንዲህ ይቀጥላል፡፡
አባወልደ ትንሳኤ ባንተ ይገኝ እንዳይነቃባቸው የሰሩትን ስራ ከታች እንመልከት ከእነሱ ጋር የተሾሙ የእነሱ አጫፋሪዎች
·         1ኛ. ሙሉነሽ አያሌው  ንብረት ክፍል  ስልክ ቁጥር 096378171? የቤንሻንጉል ጉምዝ ግልገል በለስ ተወላጅ ናት የምትኖረው ቀበሌ 06 ነው፡፡
·         2ኛ. መላክ ማማሩ  ሂሳብ ሹም  ስልክ ቁጥር 0948265441 የጁቤ ተወላጅ ቀንደኛ ቅባት እንደሆነ ይታወቃል የሚኖረው ከእነ ሳሙኤልና አቤል ገበየሁ ከመንትዮች ወንድደቾች ግቢ ዶርም ነው
·         3ኛ. አበቡ አማረ በጐ አድራጐት ክፍል  ስልክ ቁጥር 0931891930 የአምበር ተወላጅ ናት የምትኖረው ቀበሌ 06 ነው
·         4ኛ. የሻለቃ ዘውዴ ድራማና ስነፅሁፍ ክፍል ስልክ ቁጥር 0931872811
·         5ኛ. ያረጋል የአባቱን ስም ስልክ ቁጥሩን አላውቀውም
·         6 / ሰናይ የአባቱን ስም ስልክ ቁጥሩን አላውቀውም
እነዚህ በፊት ከዘረዘርናቸው 6 ልጆች ጋር ሆነው //ቤቱን ከነድራሹ ለማጥፋት የተተከሉ እሾኆዎች ናቸው፡፡ ይላል የመረጃ ምንጨ፡፡  አስከቀጥሎም ማሳሰቢያ በማለት እንዲህ ይላል፡፡ በመልእልተ አድባር ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ማርቆስ ሰንበት ትምህርት ቤት ተምረን ያደግን ልጆች ምነው እንደዚህ አድፍጠን ዝም ያልን? በቅዱስ ማርቆስ ስም ይህንን ሰንበት ትምህርት ቤት ልንታደገው ይገባል:: ይገባል በማለት ማሳሰቢያ እና ምክር ይለግሰናል፡፡ እነዚህን በአባ ወልደ ትንሣኤ ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ ታላቁን ሰንበት ትምህርት ቤት ለመበተን የተነሡ ልጆችን ወላጆች ምከሩ የምታውቋቸው ስለሁኔታው አስረዷቸው፡፡ እገሌ እኮ ጥሩ ነው በስህተት ነው የምትሉ ካላችሁ ከነማስረጃው መላክ ትችላላችሁ፡፡
የፎቶ የድምጽ የምስል ማስረጃዎችን እየቀረጻችሁ ላኩልኝ፡፡ እነዚህን ወደ በጎ አመለካከት መመለስ ይገባናል፡፡

ዘመነ ማርቆስን ለቤተክርስቲያናችን እናድርገው፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

አባ ወልደ ትንሣኤ ባንቲገኝ VS መልእልተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ ሰ/ት/ቤት

ዛሬ ጥቅምት 5/2010 ኣ.ም ነው፡፡ ============================= ·          ጸለተ ምሕላው እንደቀጠለ ነው፡፡ ·          ጽጌን በቤተክርስቲያን እያደርን በረከተ ሥጋ ወነ...