ዘሬ መስከረም 29/ 2010 ዓ.ም ነው፡፡
=======================
የምሥራቅ
ጎጃም ምእመናን ይበልጥ ውስጣቸው ነዷል፡፡ ችግር ይፈታሉ የተባሉቱ ቅዱሱ ፓትርያርክ ይኸው ላችሁ የአባ ማርቆስን ተምህርት ተቀበሉ ካልተቀበላችሁ የራሳችሁ ጉዳይ ነው በማለት ሲያቀረሹብን
ዋሉ፡፡ ዕለቱ ቅዳሜ ነው ቀኑ 27 መድኃኔዓለም መስከረም ሊገባደድ
3 ቀናት ብቻ የቀሩበት ዕለት አባ ማትያስ ልጆቻቸው የተባሉትን በሙስና እና በክህደት የተዘፈቁትን ጳጳሳት እና ሥራ አስኪያጆች
አስከትለው (የተወሰኑት ግን ነጻ ናቸው) ህንጻ ሊመርቁ በቦታው ተገኙ፡፡
አቡኑ በአጋዚ ወታደር ታጅበው ወደ ከተማዋ የገቡት በ26 ሰርክ ሰዓት አካባቢ ነበር፡፡ አይ አባ ማትያስ ሌባ እና ከሐዲ አስከትለው
ከታላቁ ሐገር ጎጃም እንዲህ ዱብ ይላሉ፡፡ ትዝ አለዎት ያኔ በሚያዝያ 2009 ዓ.ም እርስዎ መፍትሔ ይሰጡናል ብለው የመጡትን ምእመናን
ከምንም ሳይቆጥሩ ሲሸኟቸው ዛሬ እርስዎም የእጅዎን አገኙ፡፡ አንድ
ፓትርያርክ በአጋዚ ወታደር ታጅቦ ሲመጣ አቡነ ቴዎፍሎስን በተመለከተበት ዓይኑ የጎጃም ሕዝብ እንዴት እርስዎን ፓትርያርከ ናቸው
ብሎ ይቀበልዎ አዩት አይደል፡፡ አንድ ምእመና ሳይገኝ በአጋዚ ወታደር እና በሥርዎ በሸጎጧቸው ከሀድያንና ሙሰኞች ብቻ ታጅበው ወደ
ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን አመሩ፡፡
ልጆችዎ
የተባሉቱ እነ አቡነ አረጋዊ የደቡብ ጎንደር ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ የሽረ እንዳ ሥላሴው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሩፋኤል የጋንቤላ እና
ደቡብ ሱዳን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቶማስ ( የባሶው ቅባቴ) የአዊ ሊቀ ጳጳስ እነ ዘራፊው ሙሰኛው ጎይቶም ያይኑ የአዲስ አበባው ሀገረ
ስብከት እነ መናፍቁ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ አረ አሳቃችሁኝ አባቴ፡፡
የሆነ ግሩፕ መፍጠር ጀመራችሁ ልበል አዎ ፈጥራችኋል እንጅ፡፡ ይህ ሁሉ ዘራፊ እና መናፍቅ ደብረ ማርቆስ መምጣት ለምን አስፈለገው
ይህ ህንጻ ይህን ያህል ሽር ጉድ የሚባልለት ግዙፍ ህንጻ እኮ አይደለም ቢሆንም የምእመናን ትጋት እንጅ የአቡነ ቅባት ትጋት እንዳልሆነ
ማዎቅ ለምን ተሳናችሁ፡፡


አጠቃላይ
የስብሰባው የምረቃው መርኃ ግብር ሂደት ከሞላ ጎደል ከንቱ ውዳሴዎች የሰፈኑበት ህንጻ ህንጻ ሲባል የዋለበት ነበር፡፡ እንደነገርኋችሁ
አቡና ማትያስ ሲመጡ አቀባበል ያደረገላቸው የከተማ ሕዝብ የለም ነበር ሰንበት ትምህርት ቤቶችን የሉም ነበር፡፡ እርሳቸው በደረቁ
እንደተቀበሏቸው እርሳቸውንም በደረቁ ነው የተቀበሏቸው፡፡ አጋዚው ግን የሆነ ሽብር የተፈጠረ ነበር የሚመስለው አይ አባት በአጋዚ
ታጅበው መጡልን እና አረፉት፡፡ በዚህ መካከል መእመናን ቢመጡ እኮ አመፀኛ ተብለው መታሰራቸው መገደላቸው ነበር ማለት ነው እንኳንም
ቀርተዋል፡፡

የምሥራቅ
ጎጃም ሕዝብ የአቡነ ማርቆስን ትምህርት መስማት አለበት ብለው እኮ ነው መመሪያ ያስተላለፉ፡፡ ለማንኛውም የጥቅምቱ ሲኖዶስ ያስተዛዝበናል፡፡
አንድ ፓትርያርክ እንዲህ ያለ ጠባብነት ሲሰብክ ማን ይሰማዋል፡፡ ከፓትርያርኩ በላይ ሆነህ አረፍከው በሉኝ ደግሞ፡፡ ሳጥናኤል መልአክ
እንደነበረ አውቃለሁ ግን እበልጠዋለሁ በቃ የሚወዳደረው ቆባችን ሳይሆን እምነታችን ነው፡፡ ወይ እኩል እምነት ይኖረን እና በምግባር
እንበላለጣለን እንጅ በእምነት የማይመስል ሰው ግን ሲጀመርም ሊወዳደረን አይችልም በጭራሽ፡፡ ሲኖዶሱ ምንም በሉት ምን መንፈስ ቅዱስ
ይመራዋልና ሀሰተኛ ሁሉ ልሳኑ ይዘጋል፡፡ አባ ማርቆስ ደጋፊዎቻቸውን ለማስፋት አዳዲስ ጳጳሳትን በተለይ ለመያዝ ሞክረዋል፡፡ የጋንቤላው
የደቡብ ጎንደሩ የሽሬው የአዊው እነ ጎይቶም እነ ኤልያስ አብርሃ ናቸው የአባ ማርቆስ ወዳጆችና ደጋፊዎች፡፡ በነገራችን ላይ የሌባ
እና የከሀዲ ስብስብ ይዘው መጡ እንዳይባሉ እነ አቡነ መልከጼዴቅን እነ አቡነ ፊልጶስን እነ አቡነ ዲዎናስዮስንም አስከትለዋቸዋል፡፡
ያም ሆነ ይህ ግን እኛ ሁሉን ነገር ቀድመን አውቀነዋል ሰሚ የለም፡፡ ይህንን ጉባዐየ ጠብቀን የነበረው ከጥቅምቱ ጉዞ ቢያሳርፈን
ተብሎ ነበር አሁን ግን ጥቅምት ላይ ያው ከባለፈው በበለጠ ሁኔታ ምሥራቅ ጎጃም አጠቃላይ አዲስ አበባ መግባቱ አይቀርም፡፡
አንድ
ነገር ረሳሁ አባታችን! አቡነ ማርቆስን ግን አያውቋቸውም ልበል ስማቸውን ለመጥራት በጣም ሲንቀጠቀጡ ተስተውለዋል እኮ፡፡ ብጹእ
አባታችሁ አቡነ ነነነነነነነነነነነነነነነነነ ኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧ ሲሉ ውለው ማን ነው አቡነ ማርቆስ ይላሉ ክክክክክክ
ዛሬ ተዋወቁ እንጅ ባይሆን፡፡ ግን ሲመስለኝ ሲመስለኝ ቤተክርስቲያኒቷን ለማጥፋት ብዙ ውጥን ሥራ አላችሁ፡፡ ከዚያም አንዱ ይኸው
አሁን ያየነው ጉዳይ ነው፡፡ ለማንኛውም የመንግሥትን የአቡነ ቶማስን የአቡነ ማርቆስን ንግግሮች ወደፊት እንደሁኔታው ሳልቆርጥ ሳልቀጥል
በሙሉ እልክላችኋለሁ፡፡
·
በነገራችን ላይ በምሥራቅ ጎጃም የተሐድሶ መናፍቅ መስራች
የሆነው ይኼነው በዚህ ጉባዔ ተሸልሟል፡፡
·
ከ700 ሺህ ብር በላይ ያበረከተው
እና የህንጻውን ዲሳይን ከመስራት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ባለው ክትትል ከፍተኛ ሥራ እየሰራ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን ምንም እንዳልሠራ
ተደርጎ ሪፖርት ቀርቧል፡፡
·
ቅባቶች መጽሐፋቸውን በይፋ
ለመሸጥ በመቻላቸው በጉንደ ወይን ወረዳ ቤተ ክህነት በኩል አቡነ
ማርቆስን ሸልመዋል፡፡
·
ከ500ሺህ ብር በላይ የጉልበት
ድጋፍ ያደረጉ የግቢ ጉባዔ ተማሪዎች በሪፖርቱ ስማቸው አልተነሳም፡፡
·
በሀገረ ስብከቱ የሚገኙት ቄስ
አበበ የተባሉ አገልጋይ በጉልበታቸው ቀን ከሌሊት ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይሉ ሲሰሩ የነበሩ እና ለህንጻው እዚህ ደረጃ መድረስ ከፍተኛ
አስተዋጽኦ ያደረጉ ሆነው ሳለ ስም አጠራራቸው በሪፖርቱ እንዳይካተት ተደርጓል፡፡
ዘመነ ማርቆስን ለቤተክርስቲያናችን ብቻ እናድርገው!
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ