ዛሬ መስከረም 30/2010 ዓ.ም ነው፡፡
መስከረም አለቀ ጥቅምት ገባላችሁ!
=========================
መስከረም 27/2010 ዓም አቡነ ማትያስ በአቡነ
ማርቆስ (ቅባቴ) ጥሪ ተደርጎላቸው ያለ ቅዱስ ሲኖዶሱ ፈቃድ ትንሹን አባ ማርቆስ (ቅባቴው አቡነ ቶማስ) አስከትለው የመምጣታቸው
ምሥጢር ምን እንደሆነ እንደ ጉድ ይተረክላችኋል፡፡ ደግሞ የተያያዘውን ቪዲዮ ተመልከቱት አደራ ያ ካልሆነ ግን ዝም ብለህ አስተያየት
እሰጣለሁ እያልክ እንደ እሳት እራት ጥልቅ እንዳትል አደራ አደራ አደራ!

ታዲያ ከቁምስና እስከ ጵጵስና ድረስ ከጎናቸው
ሳይለዩ በቅባት የተዋወቁትን አባ ማርቆስ ምስራቅ ጎጃምን በቅባታቸው እንዲያባብሱ ከህዝቡ ጋራ በግድ ሊስማሙ ደብረ ማርቆስ ከተማ
የመጡት የአዊው አቡነ ቶማስ ቅባቴ ምን አሉ መሰላችሁ “ለቅዱስነታቸው ብዙ ወሬ ይወራላቸው ነበር ዛሬ ግን በዓይናቸው አዩት በጆሯቸው
አይደለም የሰሙት ዛሬ ዓይተውታል፡፡ ሰውን የሚገልጠው ሥራው ነው ወሬው አይደለም አለባበሱም አይደለም” ምናምን ምናምን ብለው ሞቱ
እንደቀረበው ውሻ ሲያላዝኑብን አልዋሉም መሰላችሁ፡፡ በአጋዚ ጦር ታጅቦ እንዲህ ያለ ድንቅ ቅባታዊ ንግግር ያደረጉት ብጹነታቸው
አቡነ ማርቆስ ማለት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት ናቸው ብለው ከጌታ ጋራ እያነጻጸሩ እና እያወዳደሩ ሲያሞጋግሷቸው ውለዋል፡፡ ይችም
ውለታ ትሁን አይ አንች እናት ዓለሜ ቤተክርስቲያን፡፡ትንሹን አባ ማርቆስ አቡነ ቶማስ ቅባቴን ባሶ ሊበን አቀባበል ሲደረግላቸው አቡነ ማርቆስ ትልቁ ቅባቴ ስጦታ ሰብስበውላቸዋል
ለካ የዚያንን ውለታ መመለሳቸው ነው፡፡ ምሥራቅ ጎጃም ጥያቄው የእምነት ነው አባ ቶማስ እና ሌሎችም ተናጋሪዎች እምነት የሚሉት
ህንጻ መስራትን ነው፡፡ አንድ ሊቀጳጳስ ህንጻ ግንባታን ከምእመናን ድህነት ጋራ አያይዞ ማስተማር ነበረበትን፡፡ በእርሳቸው ቤት
የባሶ ተወላጅ ስለሆኑ ብቻ የተናገሩትን ሁሉ አሜን ብሎ የሚቀበል የደብረ ማርቆስ ህዝብ ያለ መስሏቸዋል ወይ ፍንክች አለ፡፡ ሲጀመር
በጦር ተከባችሁ መምጣታችሁ አሳፍሮን ስለነበር ከእናንተ ምንም ነገር ፍሬ ያለው ትምህርት አልጠበቅንም ነበር፡፡ እኔስ ደግሞ የሚገርመኝ
በዚያ በጋንቤላው ሊቀ ጳጳስ በአባ ሩፋኤል የሚመረው ሲንቦጫረቅ የዋለው ጭብጨባ ነው፡፡ አጨብጫቡ ሁላ ጥቅምት ሲኖዶስ መድረሻህን
ያሳጣሃል፡፡ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ቢደረድሩት መፍረሱ አይቀርም በእምነት በምግባር ማነጽ ግን ምንኛ መታደል ነበር፡፡ ነገር ግን
ምእመናንን ለማነጽ የሚያበቃ ምግባርም እምነትም የሌላቸው ሰዎች መድረክ ላይ እየወጡ አባ ማርቆስን ተቀበሏቸው እያለ እንደ ቁራ
መጮኹ ትንሽ ያሳፍራል አረ በጣም ያሳፍራል የምን ትንሽ ነው፡፡
ለማንኛውም #አዊዎች ዝም ብላችሁ አትበሉ እውነቱን
እውነት ብላችሁ አባ ቶማስን ተቃወሙ፡፡ በጥቅምት ሲኖዶስ ምሥራቅ ጎጃምን ሊሰጡ ይችላሉ ብለን እንገምታለን፡፡ ይህንን የምንልበትም
ምክንያት አባ ቶማስ የአባ ማርቆስን ራዕይ የሚያስቀጥሉ ትንሹ ቅባቴ ናቸውና ነው፡፡ አዊ ላይ እምነትህን ጠብቅ ብለው ቢያስተምሩህ
እምነትህ ተዋሕዶ ስለሆነ እንዴት ያሉ መምህር አገኘን ትል ይሆናል ምሥራቅ ጎጃም ላይ ግን እምነትህን ጠብቅ ማለት ቅባትነትን ወይስ
ተዋሕዶነትን ግራ ያጋባሃል፡፡ #አዊዎች እስኪ አቡኑ ሲያስተምሩ ቀርጻችሁ ላኩልኝ፡፡ አንድ ነገር ለ #አዊዎች ልናገር አባ ቶማስ
ሲያስተምሩ #ተዋሕዶ ብለው ያውቃሉ ወይ፡፡ እባካችሁ ልብ ብላችሁ አፋቸውን ጠብቃችሁ አዳምጡ፡፡ የሚቀረጸውን ቅረጹ የሚጠየቀውን
ጠይቁ፡፡ እርስዎን ቅባት ነዎት እያሉ ሰዎች ይናገራሉ ይህ እውነት ነው ወይ ብላችሁ ጠይቋቸው ይህንንም ከፈራችሁ #ተዋሕዶ እና
#ቅባት ልዩነታቸው ምንድን ነው ብላችሁ ጠይቃችሁ መረጃ ያዙ፡፡
አባ ቶማስ በመጨረሻም ለአቡነ ማርቆስ ቅኔ ቢጤ
ተቀኝተውላቸዋል፡፡ ክክክክክክ አይ መወዳደስ አይ ከንቱ ውዳሴ መሻት አይይይ አምላክ ፊት ምን እንል ይሆን፡፡ ይህ የሽንገላ ከንፈር
ሁሉ ዲዳ የሚሆንበት ዘመን ይመጣል ያኔ የት እንገባ የት እንሸሸግ ይሆን፡፡
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ተመስገንም በጊዜው ሪፖርት
አቅርቧል፡፡ አባ ማርቆስም ስላወደሷቸው በሞቅታ ተነሥተው ተናግረዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ሙሉ መረጃ ነው ያ ብቻ እናንተ በትእግሥት ጠብቁኝ፡፡
በነገራችን ላይ የጽጌ ጾም ነበር የምረቃው ጊዜ፡፡ ብዙ ሰንጋዎች እንደታረዱ ሰምተናል መረጃው ያላችሁ ፎቶ ቪዲዮ ያላችሁ ላኩልን
በውስጥ መስመር፡፡
https://www.facebook.com/metshetewahido/videos/pcb.1931167643767496/1931166993767561/?type=3&theater
ዘመነ ማርቆስን ለቤተክርስቲያናችን ብቻ እናድርገው!!!
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ