ዛሬ ጥቅምት 1/2010 ዓ.ም ነው፡፡
#ጥቅምት_ባተልን_ይኸው!
#ወይ_ያልፍልናል_ወይ_ያልፍብናል!
============================
• በነገራችን ላይ ሁሉም ወደ ጸሎት ግንባር እንዲሰለፍ ጥሪ ተላልፏል፡፡
• ሁሉም ሰው ስለቤተክርስቲያናችን ፈተና በጸሎቱ እንዲተጋ ለዚሁ ሲባልም ከምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ በመላው ዓለም ያለ ክርስቲያን ሁሉ ለጸሎት እንዲቆም ተነግሯል፡፡
• የቻለ ቆሞ ይጸልይ ያልቻለ ገዳማውያኑን ያሳስብ ተብሏል፡፡
ወደ ዛሬው ዘገባችን ስናመራ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ መስገን ምን አሉ የሚለውን እናገኛለን፡፡ አቶ ተመስገን በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ስብሰባ ማን ማን እንደተገኙ እና በቤተክርስቲያኒቱ ምን ኃላፊነት ላይ እንዳሉ ሳይቀር በዝርዝር ነበር የተናገሩት፡፡ የዚህን አጠቃላይ ንግግር በቪዲዮው የተያያዘላችሁ ስለሆነ እርሱን ተመልከቱት፡፡ በእውነት አቶ ተመስገን ወይ በቤተክህነት ያደገ ነው አልያም ደግሞ ሪፖርቱን የጻፉት የእነአባ ማርቆስ ቡድን ነው፡፡ ይህ በሚገባ ለሁሉም ግልጽ ነው፡፡ አቡነ ቶማስ (ትንሹ አባ ማርቆስ) የመንግሥት አካል እንኳ ሲናገር በቤተክህነት የተማረ ሰው እንጅ የመንግሥት ሰራተኛ አይመስልም ብለው ያሞካሹትም ሪፖርቱን አቶ ተመስገን ስላነበበላቸው ነው እንጅ ስለጻፈው አልመሰለኝም፡፡ ለማንኛውም ግን እርሱ በትክክል የጻፈውን አንብቦ ከሆነ አቶ ተመስገንን አጨብጭቡለት በእውነት እንዴት ያለ ገለጻ መሰላችሁ ያደረገው፡፡ አቶ ተመስገን ሲጀምር በስብሰባው የተገኙትን በሚከተለው ቅደም ተከተል ነበር የዘረዘራቸው፡፡
1. ብጹ አቡነ ማርቆስ በኢትዮፕያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርቲያን የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ኃላፊ፤ የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ቦርድ ሰብሳቢ እና የምሥራቅ ጎጃም ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
2. ቅዱስ ብጹእ አቡነ ሩፋኤል የጋንቤላ ክልል የሰላም አምባሳደር የደቡብ ሱዳን እና የጋንቤላ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
3. ብጹእ ዶክተር አቡነ አረጋዊ የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
4. ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የሽረ እንዳ ሥላሴ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
5. አቡነ ዲዎናስዮስ የአሶሳና መተከል ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
6. አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
7. ብጹእ አቡነ ቶማስ የአዊ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
8. አቡነ ፊልጶስ ደቡብ ኦሞ ጅንካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
9. ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትንሣኤ ዘጉባዔ ማተሚያ ቤት ኃላፊ
10. መጋቢ ካህን ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም የጠቅላይ ቤተክህነት መጋቢ ካህናት ኃላፊ
11. መምህር ጎይቶም ያይኑ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪጅ
12. ሊቀ ማእምራን ቆሞስ አባ እንባቆም ጫኔ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪጅ
13. የአዲስ አበባ እና የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የአድባራት እና የገዳማት አስተዳዳሪዎች
14. በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሥር ያሉ የዐሥራ ሰባቱ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪጆች
15. የምእመናን ተወካይ የሀገር ሽማግሌዎች
16. የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ነበሩ፡፡
17. ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ በስብሰባ እንደተገኙ ተገልጸዋል፡፡
በጣም የገረመኝ አቶ ተመስገን ስለ አቡነ ቴዎፍሎስ ሰጠው ታሪካዊ መግለጫ ብዙዎቻችንን አስደምሟል፡፡ ግን እርሱ የጻፈው ነው አይመስለኝም አይመስለኝም አልኩ አይደል አረ እውነቴን ነው፡፡ የመንግሥት አካል ምንም ይሁን ምን ንግግስ ሲያደርግ ራሱን በሃይማኖቱ ውስጥ አስገብቶ እኛ እያለ ተናግሮ አያውቅም ይህ አስተዳዳሪ ግን በቃ ጽሑፉ የቤተክህነቱ በሚመስል መልኩ ስላቀረበው እኔ በራሴ ተገርሜበታለሁ፡፡ ግን የእሱ ነው? አረ አዳምጡት፡፡
መልአከ ብርሃን አድማሱን፤ አለቃ አያሌው ታምሩን፣ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤን፣ አለቃ ተክል ኢየሱስ ዋቅጅራን፣ እማሆይ ገላነሽን፤ ዐራት ዓይና ጎሹን፣ ሐዲስ አለማየሁን፣ ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራውን ጠቅሶ እኮ ነው በአባ ሩፋኤል የሚመራውን ቦጭራቃ ጭብጨባ ያስጨበጨበው፡፡ አልዋሽም እኔም ብኖር ለተመስገን ግን አጨበጭብለት ነበር በእውነት በእውት ስላችሁ፡፡ ደግሞ መንግሥትን ፈርተህ ነው እንዲህ ያልክ ብላችሁ አስወሩ መቸም ወሬ አያልቅባችሁም፡፡
ግን አቶ ተመስገን አስተዳዳሪው በጣም የዘነጉትን ነገር ሳላሳስብ ከፌስቡክ አልወርድም በእውነት አልወርድም፡፡ የዞኑ ጸጥታ እኮ አቡነ ማርቆስ እያደረጉት ያለው ነገር ለዞኑ የጸጥታ ስጋ እንደሆነ በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ዞኑ የጻፈውን ደብዳቤ ከዚህ በታች አብሬ አያይዠላችኋለሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቪዲዮውን የሠራሁት በዚሁ ደብዳቤ ስለሆነ ከቪዲዮውም ማንበብ ትችላላችሁ፡፡ አቶ ጌትነት አንለይ የተባለው የዞኑ ጸጥታ ዘርፍ እውነቱን ሳይሸፋፍን ሳይደባብቅ በግልጽ ነው የጻፈው፡፡ የዚህ ደብዳቤ ግልባጭም ለአቶ ተመስገን ደርሷል ይህ ምንም የማይካድ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አብርሃም በከተሞች መድረክ ላይ እኮ የተናገረውን ብትሰሙ ትገረማላችሁ ታዲያ ዛሬ አቶ ተመስገን ምን ነካህ ሳልልህ አላልፍም፡፡ በአባ ማትያስ ፊት እውነቱን ለመመስከር ማን ፍርሐትን ፈጠረብህ ብየ መጠየቄን አላቆምም፡፡ የአቶ አብርሃምን ንግግር አብሬ አያይዠላችኋለሁ ይህ በከተሞች መድረክ ላይ የተነገረ ነው፡፡ ሁሉም የሰማው አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው፡፡ አቶ ተመስገን ግን የሆነ ፍርሐት ያለበት ነው የመሰለኝ፡፡ ይህ የጻፈውም ተመስገን አይደለም እንድል ያደረገኝ ይኸው ጉዳይ ነው፡፡ ዞኑ ላይ የጸጥታ ችግር እየተፈጠረ ያለው በአብዛኛው በአቡነ ማርቆስ በሚመራው ሀገረ ስብከት ስር ባሉ አብያተ ክርስቲያናት እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ ታዲያ ተመስገን ዛሬ ምን ነክቶት ነው፡፡ መረጃውን አዳምጡት፡፡
https://www.facebook.com/metshetewahido/videos/pcb.1931538320397095/1931535490397378/?type=3&theater
https://www.facebook.com/metshetewahido/videos/pcb.1931538320397095/1931536430397284/?type=3&theater
በስብሰባው ስለተገኙት ግን ትንሽ ብንል ሳይሻል ይቀራል፡፡
1. አቡነ ዲዎናስዮስ የአሶሳና መተከል ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ
2. አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
3. አቡነ ፊልጶስ ደቡብ ኦሞ ጅንካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፡፡
እነዚህ በሀምሌ 9/2009 ዓ.ም የተሸሙት አዲስ ሊቃነ ጳጳሳት ሲሆኑ የአቡነ ማርቆስን የጥፋት ዕቅድ የማይደግፉ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከአቡነ ማትያስ እና ከአቡነ ማርቆስ የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው በቦታው የተገኙ ናቸው፡፡ በመገኘታቸው ከእነ አቡነ ማርቆስ የጥፋት ቡድን ጋር እንዳትቀላቅሏቸው እነዚህ አባችስ ወዲያው እንደተሸሙ ነው ወዮልሽ ተሐድሶ ብለው ተሐድሶን በማውገዝ ሥራቸውን የጀመሩት፡፡ ምሥራቅ ጎጃም በመወለዳቸው እና እዚህም በመማራቸው ቦታውን ለመመልከት ስለመጡ እናመሰግናቸዋለን፡፡ እነዚህን አባቶች አደራ ከእነ አቡነ ማርቆስ ቡድን ጋራ ቀላቅላችሁ እንዳትጨፈልቋቸው፡፡

በውስጥ መስመር ስለ አቡነ ማርቆስ የደረሰኝ መረጃም አለ እርሱን ምንም ሳልጨምር ሳልቀንስ እነሆ ብያለሁ!!!
መስከረም 29 የቅድስት አርሴማ ዓመታዊ በዓል በቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን የፅጌ ፆም ሰጋ በልተን የምናገግምበት፣ማገገሚያ ነው እባካችሁ የሰ/ት/ቤት ወጣቶች ጾም ጹሙ እያላችሁ አታስቸግሩ እያሉ ሲቀባጥሩ የነበረውን የክህደት ትምህርት ፣ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ ጥያቄ አቀረባችሁ በሚል ጠንካራ የሆኑ የሰ/ት/ቤት ወጣቶች የቅባቴው ቀኝ እጅ በሆኑት በመ/ፀሐይ አባ ወልደ ትንሳኤ ባንተይገኝ አማካኝነት መሪ እንደሌለው መንጋ የበተኗቸው የሰ/ት/ቤት ወጣቶችን የስድብ ውርጅብኝ ሲያፈሱ ቀይ ካርድ ቀይ ካርድ እያሉ ሲንቀለቀሉ ፣በስርዓተ ቅዳሴው ስዓት ሲሳደቡ የነበረውን እንዲሁም የቅባቴው ቀኝ እጅ የሆኑት መ/ፀሐይ አባ ወልደ ትንሳኤ ባንተይገኝ ከጭፈራ ቤት አምጥተው የሾሟቸውን እነ ፀጉረ ጨብራራን መስፈርቱን አሟልተው በሰ/ት/ቤት የተመዘገቡ አገልጋዮት እያሉ ሲያሞካሹ በተጨማሪም የቅዱስ ማርቆስ ስንበት ትምህርት ቤት ከቀኑ 12፡30 በኋላ ጭፍራ ቤት እንደሚመስል የእነ ጭፍራ ቤቱ ፀጉረ ጨብራራና የቅባቴውን አትፁሙ የሚለውን የክህደት ትምህርት የቅባቴውን ቀኝ እጅ አንጋፋውን ቅዱስ ማርቆስ ሰ/ት/ቤት ያፈራረሱትን አሁን እንደፈለጉት የሚገጋሉቧቸው የጭፈራ ቤት ወጣቶችን የሾሟቸውን መ/ፀሐይን ጉድ አውጣው እንጅ ከነፎቶአቸው መረጃውን ልቀቀው

ቅባቴው መስከረም 29 ቀንማ መጦባቸው ነበር ባል ወይም ሚስት ካገቡ በኋላ ሰ/ት/ቤት ገብቶ ማገልገል መጃጃል ነው እያሉ ኸረ ስንቱ
መረጃ የሰጡኝን በጣም አመሰግናለሁ፡፡ በነገራችን ላይ ማንኛውንም ዓይነት መረጃ አድርሱኝ ስለቤተክርስቲያን መጨነቅ አለብን፡፡ የ666 ትኩረት የሆነችው አገር ማን መሰለቻችሁ የእኛ አገር እኮ ናት ቤተ ክርቲያን ደግሞ ዋናይቱ ናት፡፡ እርሷን ከያዙ መላውን ዓለም የ666 ተገዥ እንደሚያደርጉት ያስባሉና ቀስታቸው ተሰብቆብናል፡፡ የዚህ አስፈጻሚ የሚሆኑትም አባቶቻችን ብለን የምንጠራቸው ናቸው፡፡
የጥቅምቱ ሲኖዶስ አንድ ነገር ያመጣልን ይሆናል ካልሆነ ግን እውነታውን ከመግለጽ አንቆጠብም፡፡
ዘመነ ማርቆስን ለቤተክርስቲያናችን እናድርገው፡፡
ዘመነ ማርቆስን ለቤተክርስቲያናችን እናድርገው፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ