እሑድ 15 ኦክቶበር 2017

አባ ወልደ ትንሣኤ ባንቲገኝ VS መልእልተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ ሰ/ት/ቤት


ዛሬ ጥቅምት 5/2010 ኣ.ም ነው፡፡
=============================
·         ጸለተ ምሕላው እንደቀጠለ ነው፡፡
·         ጽጌን በቤተክርስቲያን እያደርን በረከተ ሥጋ ወነፍስን እንሸምትበት፡፡
·         ሲኖዶሱ እሁድ ጥቅምት 12/2010 ዓ.ም በጸሎት ይከፍታል፡፡
·         በየወረዳው አቡነ ማርቆስን እንዲነሡልን የሚጠይቁ የተዋሕዶ ልጆች ተባራክተዋል፡፡
·         በተሐድሶዎቹ ላይ የተያዘው አቋም እንዲበረታታ ቅዱስ ሲኖዶስን የሚጠይቅ የህዝብ ፊርማ እየተሰባሰበ ነው፡፡
·         ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን ቅዱስ ሲኖዶስን በይፋ ይቅርታ ጠይቀች እነ ዳግማዊ ደርቤ እና ሃብታሙ ሽብሩም የምርትነሽን መንገድ እንደሚከተሉ አሳውቀዋል፡፡
·         አባ ወልደ ትንሣኤ ባንቲገኝ የመልእልተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ ሰ/ት/ቤትን ለማዳከም እየሠሩ እንደሆነ መረጃ ደርሶኛል ወደዚሁ እንለፍ፡፡



ሐሙስ 12 ኦክቶበር 2017

አቡነ ማርቆስ VS ምሥራቅ ጎጃም ምእመናን አቡነ ማርቆስ VS ምሥራቅ ጎጃም አስተዳድር ጽ/ቤት አቡነ ማርቆስ VS ሰንበት ትምህርት ቤት አቡነ ማርቆስ VS ማኅበረ ቅዱሳን

አቡነ ማርቆስ VS ምሥራቅ ጎጃም ምእመናን
አቡነ ማርቆስ VS ምሥራቅ ጎጃም አስተዳድር ጽ/ቤት
አቡነ ማርቆስ VS ሰንበት ትምህርት ቤት
አቡነ ማርቆስ VS ማኅበረ ቅዱሳን
ዛሬ ጥቅምት 3/2010 ዓ.ም ነው፡፡
==============================
·         ጸሎተ ምሕላው እንደቀጠለ ነው፡፡
·         አቡነ ማርቆስ የምሥራቅ ጎጃም ዞን አስተዳድር ጽ/ቤትን የተሳደቡበት በድብቅ የተቀረጸ መረጃ ይፋ ሆኗል ወደፊት በትእግሥት ጠብቁኝ፡፡
·         በደብረ ማርቆስ ከተማ የሚገኘው የመልእልተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ ሰንበት ትምህርት ቤት በአባ ወልደ ትንሣኤ እንዲዳከም አድርገው የተኳቸውን የሰንበት ትምህርት ቤት ሥራ አስፈጻሚዎችን ከነ ሙሉ መረጃቸው ደርሶኛል ይህንንም በትእግሥት ጠብቁኝ፡፡
ብጹእ አቡነ ማርቆስ በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ከመጡበት 2004 ዓ.ም ጀምሮ ከምእመናን ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲገጥማቸው እስካሁን ድረስ አሉ፡፡ ይህን ሀገረ ስብከት ከተረከቡበት ጀምሮ ምእመናን ተቃውሟቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ሲያሰሙ ቆይተዋል አሁንም ድረስ በማሰማት ላይ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በ2005 የነበረውን ተቃውሞ የፊርማ ማሰባሰቢያ ደብዳቤ እንዲህ ይመለከታል፡፡
==========================================================================================

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ቀን፡- ኅዳር30/2005 ዓ.ም
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ 
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
ከሁሉም በፊት የሀገረ ስብከቱን ምእመናን አቤቱታ ለመስማት በመፍቀዳችሁ በእግዚአብሔር ስም እያመሰገንን እኛ በሀገረ ስብከቱ በተለይም በደብረ ማርቆስ ከተማና አካባቢው የምንኖር የቤተክርስቲያን ልጆች በሀገረ ስብከቱ የተከሰቱትንና እየተከሰቱ ያሉትን ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ ችግሮች ለመፍታት ከብፁዕነታቸው ጋር የመንግስት ከፍተኛ የአመራር አካላትንም በመጨመር ተደጋጋሚ ውይይት ለማድረግ የሞከርን ቢሆንም ብፁዕነታቸው በሚያሳዩት አባታዊ ያልሆኑ ንግግሮች ውጤታማ ሊሆን አልቻለም፡፡ እኛም የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ተሰባስበን በመወያየት የቤተክርስቲያኒቱን እሴት የሚያንኳስሱ ክንዋኔዎች፤አሠራሮችና ሁኔታዎች ከዕለት ዕለት እየበዙ በመምጣታቸው ጉዳዩን ለቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አካል ለቅዱስ ሲኖድስ ሰላማዊና ተቋማዊ መዋቅሩን በጠበቀ መልኩ ይኸው ዛሬ ለማቅረብ ተገደናል፡፡
ምክንያቱም፡-

í) በሀገረ ስብከታችን እየተከሰቱ ያሉ አስተዳደራዊና ሃይማኖታዊ ችግሮችን ከምንጩ ለማስረዳት፤
î) አሁን የተከሰቱትና እየተከሰቱ ያሉት ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ ችግሮች ምንም መፍትሔ ሳይበጅላቸው በዚህ አካሄድ ከቀጠሉ ለሀገረ ስብከታችን እና ለመላ ቤተክርስቲያናችን ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን ሊያስከትል የሚችል በመሆኑ ከወዲሁ መፍትሔ እንዲፈለግበት፤
ï) ሀገረ ስብከታችን ልዩ ትኩረት የሚያስፈልገው “ከቅባት” ጋር የተገናኙ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቻችንና መላ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ልዩ ትኩረት እንዲሠጡት ለማስገንዘብ ሲሆን ብፁዕነታቸው አቡነ ማርቆስም በተደጋጋሚ ራሳቸውን ከሁሉም የተለዩ ፣የማይገኙ ፣ የማይተኩ ፣ እሳቸው ያሉትን የማይቀበል ያልዳነና ያልገባው መሆኑን በመግለጽ ካህናቱን በመሳደብ፣ ምእመኑን ወንጌል ያልገባው በደብተራ የተተበተበ እና ሌሎች የንቀት፣ የስድብ እና የእርግማን ንግግሮችን በመናገር የበደሉን በመሆኑ ለችግሮች መፍትሔ ለማፈላለግ እንጂ አቤቱታችን ከጭፍን ጥላቻና ነቀፌታ የነፃ ፍጹም ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ መፍትሄን በመሻት ነው፡፡
         

        íኛ. አስተዳደራዊ ችግሮች
ብፁዕነታቸው አቡነ ማርቆስ ወደ ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት እንደመጡ ብዙ ጉዳዮችን በትችት ሕዝቡንም በንቀት የተመለከቱ ሲሆን በመጡ በ3ኛ ወራቸው ጀምረው፡-
í)  ከ41 በላይ ሹም ሽርና እገዳ ያካሄዱ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሹም ሽሮችና እገዳዎች ሕገ ቤተክርስቲያንን /ቃለ አዋዲውን/ ያልተከተሉ፤ተቋማዊ መዋቅሩን የጣሱ ይገኙባቸዋል፡፡
î) ቅድስት ቤተክርስቲያን በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ በቃለ ዓዋዲው መሠረት የተቋቋሙትን ሰ/ት/ቤቶችን “ወንበዴዎች፤ሌቦችና አሸባሪዎች” በማለት በሕዝብ ፊት ተሳድበው ለሰዳቢ ሠጥተዋል፡፡
ï በንጹሐን ምእመናን ላይ ሰብአዊ ክብርንና ነፃነትን የሚጋፋ የስድብ፤ንቀትና እርግማን አካሄደዋል፡፡
ð ) ብፁዕነታቸው ከሦስት በላይ መኖሪያ ቤቶች ያሏቸው ሲሆን ከእነዚህም መካከል ተወልደው ባደጉበት፣ በተማሩበትና ባስተማሩበት ጉንደወይን ከተማ /በ2004 ዓ.ም የተገዛ/ እና አዲስ አበባ / በ2000 ዓ.ም የተገዛ/ ያላቸው ሲሆን ከአዲስ አበባው መኖሪያ ቤት የግንባታ ውል ክፍያ ጋር በተያያዘ በብፁዕነታቸው በብፁዕ አቡነ ማርቆስ ላይ የተፈጸመው ክስና እስራት በሀገረ ስብከታችን ያሉትን ምእመናንን አንገት ሰብሯል፤ አዋርዷል፡፡ በዚህም ወቅት በሀገረ ስብከታችን አስተዳደር ውስጥ በሂሳብ ሹም፣ ገንዘብ ያዥና መዝገብ ቤት መካከል  ሦስት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በአንድ ቀን የተደረጉ ለውጦችና ሰዎቹ ለብፁዕነታቸው ካላቸው ዝምድናና አካሄድ አንጻር ነገሩን ለሀገረ ስብከቱ ምእመናን ከጥቂት ዓመታት በፊት በብፁዕነታቸው አቡነ ዘካርያስ ከተፈጸመብን በደል አንጻር እንቅስቃሴውን እንቆቅልሽ  አድርጎብናል፡፡

                         
îኛ. ሃይማኖታዊ ችግሮች
ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ወደ ሀገረ ስብከታችን ከመጡበት ከኅዳር 2004 ዓ.ም ጀምሮ በካህናት፤በዲያቆናትና በሌሎች የቤተክርስቲያኒቱ ምእመናን ዘንድ ያልተለመዱ፤እንግዳ ክንዋኔዎች እየተስተዋሉ ሲሆን ክንዋኔዎቹና አሠራሮቹም ምእመናንን ግራ ያጋቡ፤ለመናፍቃንም በር የከፈቱና የሚከፍቱ ናቸው፡፡

ከእነዚህም መካከል ፡-

1 ) ብፁዕነታቸው አቡነ ማርቆስ ከመጡ ከሁለት ወራት በኋላ ጀምሮ የቅድስት ቤተክርስቲያናችን ቅዱሳን አበው ለመናፍቃን መልስ የሰጡበትና ለአማኞች ያስተማሩበት ሃይማኖተ አበው መጽሐፍ ‹‹እኔ ልማታዊ ነኝ ጊዜውን በአግባቡ መጠቀም አለብን›› በሚል ተገቢ ያልሆነ ምክንያት ከቅዳሴ በኋላ እንዳይነበብ ተደርጓል፡፡



)2 በአንዳንድ አድባራትና ገዳማት በውል በታወቀ ምክንያት የቅዳሴ ጸሎት ሰዓቱ ቢቀየርም በፍትሐ ነገስት አንቀጽ 12 ላይ ‹‹ሕዝቡ ሳይሰበሰቡ የቅዳሴውን ጸሎት አይጀምሩ›› የሚለውን በመተው በሀገረ ስብከታችን ለብዙ ዘመናት ምቹ ከሆነው ንጋት የ12፡00 ሰዓት የቅዳሴው ጸሎት ያለ ምንም ተጨባጭ ምክንያት ‹‹ሰዓቱን ለወንጌል መጠቀም አለብን›› በሚል ምክንያት ወደ 11፡00 ሰዓት እንዲሆን ተደርጓል፡፡በዚህም እናቶች፤እህቶች፤ሕጻናትና አረጋዊያን ሌሊት 10፡00 ሰዓት ከቤታቸው እንዲወጡ በመገደዳቸው መቸገራቸውን፤መማረራቸውንና በቅዳሴ ሰዓትም የምእመኑ ቁጥር መቀነሱን እንገልጻለን፡፡
 3)  በክብር ለቡራኬ በእጃችን በማድረግ እንቀበለው የነበረውን የቅዳሴ ጸበል ያለ ምንም ምክንያትና ጥቅም ብፁዕነታቸው በጆግ በማደረግ በጅምላ ምዕመናንን መርጨት በማዘውተራቸው ምእመናንም ሲጠይቋቸው ‹‹እንግዲያውስ አረቄና ጠላ ልርጫችሁ?›› በማለት የተዘባበቱና የመለሱ ሲሆን ነገና ከነገ ወዲያ ይህ አካሄድ ወደ ቅዱስ ቁርባኑ የማይሄድበት ምንም ተጨባጭ ምክንያት እንደማይኖር እንገልጻለን፡፡
 4) በቅዳሴ ጸሎት ጊዜ ታቦተ መንበሩን ለምእመናን ግልጥ ሆኖ እንዲታይ በማስገደድ (ካህናቱ ሥጋውና ደሙን ሲፈትቱ እንዲታይ በማድረግ) በአካባቢው ሽማግሌዎች አበባል ‹‹የኢትዮጵያ ሙሽራ ዛሬ ተገለጠ ክፉ ቀን መጣ›› እስኪባል ድረስ ብዙ ተቃውሞ ቢገጥማቸውም በቤተክርስቲያናችን ያልተለመደ የጸሎተ ቅዳሴ ሥርዓት እንድንከተል እየተገደድን እንገኛለን፡፡
 
5) በቅድስት ቤተክርስቲያናችን የሥርዓት መጽሐፍት በሆነው በፍትሐ ነገስት መሠረት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጾሙን ወራት በሚታሰብበት በጾመ ኢየሱስ ወይም ቢይ ጾም በአርምሞ፤በጾምና በጸሎት፤በንስሐና ቅዱስ ቁርባን፤በሱባኤ የጌታን ሕማማተ መስቀል እያሰቡ ማዘን፤ማልቀስ የሚገባ በመሆኑ ከበሮ የማይመታ የማይጨበጨብ ቢሆንም ብፁዕነታቸው ይህንን ሥርዓት በመተው ምእመናን “አልለመድንም ከበሮ አንመታም አናጨበጭብም” ቢሉም ‹‹እኔ ሊቀ ጳጳሱ ተቀምጬ፤እኔ ፊታችሁ እያለሁ›› በማለት በደ/ማርቆስ ከተማ በሚገኘው ጽርሐ ጽዮን አብማ ማርያም ቤተክርስቲያን በተደረገ ጉባኤ ምእመኑ ሳይፈልግ በማስገደድ ከበሮ አስመትተዋል፤ አስጨብጭበዋል፡፡
  )6 ካህናት ምእመናንን በተለይም የንስሐ ልጆቻቸውን በቅርብ መከታተል ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህ መሰረት ካህናቱ በየንስሐ ልጆቻቸው ቤት በመዘዋወር ቡራኬ ይሰጣሉ፡፡ ብፁዕነታቸው ግን የሀገረ ስብከቱን ካህናት ክብርን በሚነካ መልኩና በጸበሉ ፈዋሽነት አለማመንን በሚያሳይ አነጋገር ‹‹ውኃ ግድግዳ ላይ ከመርጨት በቀር ወንጌል የማያውቁ›› በማለት ተሳድበዋል፡፡ ጸበል ውኃ ብቻ ነውን? ካህናቱስ አይባርኩትምን? እርሱስ መጻጉዕ የተፈወሰበት ወንጌል አይሆንም? ካህናቱስ ሌላ አያውቁምን?
)7 በፍትሐ ነገስት አንቀጽ 14 ላይ በተገለጸው መሠረት ሴት በወር አበባ(በወርኃ ጽጌ) ወቅትና አራስ ስትሆን ቤተክርስቲያን መግባትን የሚከለከል እንደሆነ ቢታወቅም ብፁዕነታቸው መግባት እንደሚችሉ የፈቀዱ ሲሆን እርሳቸው በተገኙባቸው ጉባኤያት ላይ ‹‹እኔ አባታችሁ እያዘዝሁ፣እኔ ፈቅጄ፣ እኔ የቤተክርስቲያኒቱ ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያው እያለሁ›› በማለት እንዲገቡ በማስገደዳቸው የተወሰኑት እናቶችና እህቶች ትዛዛቸውን አክብረው ሲገቡ ቀሪዎቹ ለቤተክርስቲያን ክብር ሲሉ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ማየት የተለመደ ትርኢት ሆኗል፡፡
 )8 ብፁዕነታቸው ከላይ በተራ ቁጥር ሁለት ከተጠቀሰው የቅዳሴ ጸሎት  ሰዓቱን እንዲሻሻል ከማድረጋቸውም በተጨማሪ በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ መውጣት እንጂ መግባት ይቻላል በማለት አባቶቻችንና ወላጆቻችን ያላስተማሩንን የማናውቀውን ሥርዓት እንድንከተል እየተገደድን መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
9)  ብፁዕነታቸው ነገረ ቅዱሳንን በተመለከተ ግራ የሚያጋባ አቋም ያላቸው ሲሆን የሀገረ ስብከቱ ሰባኪያነ ወንጌልን በመንበረ ጵጵስና ሰብስበው ‹‹ክርስቶስን ስበኩ እንጂ አቡሀይ እሙሀይ አትበሉ›› በማለት ስለ ቅዱሳን ያላቸውን አመለካከት ተናግረዋል፡፡
     
 በአጠቃላይ በሀገረ ስብከታችን ብፅዕነታቸው ያደረሱብን ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ በደል እኝህ ብቻ ሳይሆኑ የተጠቀሱት ማስረጃ ማቅረብ የሚቻልባቸው ሲሆኑ በዚህ ጹሑፍ ቢቀርቡ የቤተክርስቲያንና የአባቶቻችንን ክብር የሚያስደፈሩ በመሆናቸው ያላቀረብናቸው ሲሆን እኛ በምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የምንገኝ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ከጥቂት ዓመታት በፊት በብፁዕነታቸው አቡነ ዘካርያስ የደረሰብን በደል ከልባችን ሳይሽር ከኃሊናችን ሳይወጣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ለችግራችን መፍትሄ ለመፈለግና ምእመናንን ለመካስ ጥረት ቢያደርጉም ጥረታቸው በብፁዕነታቸው መቀጠል ሲገባውና የደረሰብንን በደል መካስ ሲገባቸው ድጋሜ ዘርፈ ብዙና መሰረታዊ ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ ችግሮች በመከሰታቸው ምክንያት ይህን ችግር ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቻችንና ለመላ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ጉዳዩን ለመግለጽ የተገደድን ሲሆን አስፈላጊውን ተቋማዊ መዋቅር ተከትለን ችግሩን ለመፍታት ጥረት ብናደርግም ባለመሳካቱና ምላሽ ባለማግኘታችን መሆኑን እየገለጽን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቻችን ይህን ጉዳይ በጥልቀትና በስፋት ተመልክተው መፍትሔ እንዲሰጡን ከዚህ ሸኝ ደብዳቤ ጋር ባያያዝነው 116 ገጽ የድጋፍ ፊርማ እየገለጽን እኛ የሀገረ ስብከቱ ምእመናን በቅዱስ እግዚአብሔርና  በቅዱሳኑ ስም እንጠይቃለን፡፡
   
“ቡራኬያችሁና ጸሎታችሁ አይለየን”
         
የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ምእመናን ተወካዮች

ግልባጭ
  •  ብፁዕ አቡነ ናትናኤል አቃቤ መንበረ ፓትርያርክ
  •  ለመንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት
  •  ለፓትሪያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት
  •  ለምሥራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት
  •  ለምሥራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደርና ጸጥታ ዘርፍ ጽ/ቤት
==========================================================================================
 https://www.facebook.com/metshetewahido/videos/pcb.1932176840333243/1932176313666629/?type=3&theater

ይህ ከላይ በ2005 ዓ.ም የተጻፈው የተቃውሞ ደብዳቤ ምንም ዓይነት ለውጥ አላመጣም፡፡ እንዲያውም ችግሮች ተባብሰው ነው የቀጠሉት፡፡ ነገር ግን ይህ ተቃውሞ በዚህ አላቆመም በ2009 ዓ.ም ተቃውሞው በከፍተኛ ደረጃ ተቀጣጥሎ መውጣቱ ለሁሉም የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡ የዚህን ተቃውሞ ፍሬ የምንመለከትበት ደግሞ የጥቅምት ሲኖዶስን ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይህንን ፍሬ ገና በአበባነቱ ለመቅጨት የሞከሩት ብጹእ አቡነ ማርቆስ በሀገረ ስብከቱ በሚገኙ ምእመናን የተገነባውን ሁለገብ ህንጻ ህንጻው ሳይጠናቀቅ ለማስመረቅ ሞክረዋል፡፡ በዚህ የምረቃ ቀን መስከረም 27/2010 ዓ.ም ቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምረው የእኔ ያሏቸውንም ጳጳሳት አስከትለው በቦታው ተገኝተዋል፡፡ በነገራችን ላይ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን በእናንተ ምክንያት የሰው ህይወት እንዲጠፋ አንሻምና በዚህ ምረቃ ቀን ፓትርያርኩ ባይገኙ ይመረጣል ብሎ ማሳሰቡን አውቀናል፡፡ የመጣው ይምጣ ብለው የህዝቡን አቤቱታ ከመጤፍ ያልቆጠሩት አባ ማትያስ ግን በአጋዚ ጦር ተከበው እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታጅበው ደብረ ማርቆስ መጥተዋል፡፡ ዋና ዓላማው አባ ማርቆስን በዚሁ ሀገረ ስብከት እስከ ዐረፍተ ዘመናቸው ድረስ እንዲቀጥሉ ለማግባባት የነበረ ሲሆን ምእመናን በቦታው ባለመገኘት ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡
ጥቅምት ሲኖዶስ ይጀመር እንጅ ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ማመልከታችን የማይቀር ነው፡፡ መቼ እንዴት ማን ይሄዳል የሚለውን ነገር ግን ለእናንተ አልናገርም ከፈለጋችሁ እናንተም ተደራጅታችሁ አዲስ አበባ እንገናኛለን፡፡ መጠየቅ ያለብንን ጉዳይ መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ደግሞ ይህንን ሰምተው እነ አባ እንባቆም እንቅልፍ እንዳያጡ ነገ ጀምረው አዲስ አበባ ነው የሚገኙት እኮ ለነገሩ አብረውም ሊሰበሰቡ ይችላሉ፡፡ ለማንኛውም እስኪ በምረቃው ወቅት አባ ማርቆስ ምን ተናገሩ ወደሚለው እንሂድ ለማንኛውም እናንተ ግን ሙሉውን ቪዲዮ ተመልከቱት እኔ ዋና ዋና ነጥቦችን ብቻ ነው የምጠቁም፡፡
1.      እኔ ትንሹ አገልጋይ ይችን ጸሪቀ መበለት የሆነች የሥራ ፍሬ ስላበረከትሁ ሁላችሁም አጨብጭቡልኝ በማለት አጨብጫቢዎችን አስጨብጭበዋል፡፡ አሁን ይኼ ትህትና መሆኑ ነው፡፡ እኔ ግን አይመስለኝም፡፡ 4፡45 ላይ አዳምጧቸውማ ትስቃላችሁ እኮ “በርባናስ” ብለው ሲናገሩ “በርናባስ” ለማለት መሆኑ ነው አይይይ፡፡
2.     ጨሞጋ ላይ ፈለገ አርዝ  ካርታ እና ፕላን አስወጣንበት ያሉት የቦታ ስፋት አዳምጡ 8፡48 ላይ አድምጧቸው 96 ሺ ካሬ ሜትር ነው አሉ ስፋቱ ትናንት በላኩላችሁ ቪዲዮ ሥራ አስኪጁ 11፡01 ላይ ሲናገሩ 64 ሺ 5 መቶ ካሬ ሜትር ስፋት ካርታ እና ፕላን አሰራን ይላሉ፡፡ አባ ማርቆስ ሥራ አስኪጃቸው አባ እንባቆም ከተናገሩት ስፋት 31 ሺ 5 መቶ ካሬ ሜትር ልዩነት አለ፡፡ ታዲያ ይህ ልዩነት ከየት መጣ ውሸት መሆኑን በዚህ አትረዱም ታዲያ፡፡ ከላይ ባስቀመጥኩላችሁ ደቂቃዎች ላይ ቪዲዮዎችን እየከፈታችሁ አዳምጧቸው በእውነት እኔ ስለገረመኝ ነው፡፡ በሰው ዘንድ የውሸት ተቀባይነት ለማግኘት አንድ ሊቀ ጳጳስ 31 500 ካሬ ሜትር ውሸት እንዴት ሊናገር ይችላል፡፡
3.     10፡35 ጀምረው ስለ ህንጻው ስያሜ ይናገራሉ፡፡ ሕንጻው ራእየ ቅዱስ ወሰማእት ቴዎፍሎስ ነው አሉና መርጡለ ማርያም ሲጠናቀቅ ደግሞ ራእየ ማትያስ እንለዋለን ብለዋል፡፡ የዚህኛውስ እስኪ ይሁን የዚያኛው ግን እንዴት ሊሆን ይችላል? መርጡለ ማርያሞች ይህን ጉድ ሰምታችኋል ግን? ይህ የሀገረ ስብከቱ ህንጻ ሁለገብ ህንጻ ስለሆነ የህንጻ ስም ሊስፈልገው ይችላል፡፡ ራእየ ቴዎፍሎስ መባሉም ትክክለኛ ስያሜ ነው፡፡ የቅዱስ ወሰማእት አቡነ ቴዎፍሎስ መታሰቢያ በጎጃም መኖሩ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ የመርጡለ ማርያሙ ህንጻ ግን ሁለገብ ህንጻ ሳይሆን ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ታዲያ ቤተክርስቲያኑን “ርእሰ ርኡሳን መርጡለ ማርያም” ገዳም” ተብሎ ይጠራል እንጅ  “ራእየ ማትያስ” ቤተክርስቲያን ሊባል ይችላ እንዴ? መርጡለ ማርያሞች የግራኝ እመቤትን ስም በአባ ማትያስ ስም ሊቀይሩላችሁ ነው አባ ማርቆስ፡፡ ቅርሱን ዘርፈው ጨረሱ በህንጻው ግንባታ ሰበብ ከውጭ አገር ድረስ ገንዘብ እየለመኑ ለራሳቸው አደረጉ ታዲያ ሰያሜውን ደግሞ ራእየ ማትያስ የሚሉት ምን ሰለሆኑ ነው? መርጡለ ማርያሞች አሁን አሁን እኮ ነቅታችኋል ይመስለኛል በፊት አካባቢ ነበር ትንሽ መምታታቶች የነበሩት አሁንማ ለይቶላቸዋል እኮ፡፡ ራእየ ማትያስ ብለው አንዱን ቤተክርስቲያን ሊሰይሙላችሁ እኮ ነው መወዳጃ ሊደርጉት ነው የተነሡ፡፡
4.     13፡18 ክቡር ሥራ አስኪያጁን አባ ዕንባቆም ነገ የቅዱስነትዎ ልጅ ይሆናል ተብለው ተሚካሽተዋል፡፡ መቼ ይበላሉ መቼ ይተኛሉ እያልሁ አስባለሁ ደማቸውን እስከማፍሰስ ደርሰዋል ለዚህ ህንጻ አሉላቸው፡፡ እያወቅን ለምን እንሸዋወዳለን አባታችን፡፡ አባ እንባቆም እኮ ደማቸውን ያፈሰሱ እርስዎን በዚህ ሀገረ ስብከት እንዲቆዩ ለማግባባት ወደ ክልል ሲሄዱ ከመኪና ጋራ ተጋጭተው ነው፡፡ አሁን በቅርቡ ደግሞ የት እንደሚሄዱ ባላውቅም ከጢቅ አለፍ ብለው ነው ከመኪና ጋር ተጋጭተው ደማቸው የፈሰሰው፡፡ ህንጻው ሲሰራ ብሎኬት አልወደቀባቸው ህንጻ አልተደረመሰባቸው ምን ሆነው ነው ደማቸው የፈሰሰው ይህ በእውነቱ ሰውን ያለአቅሙ መቆለል ይመስለኛል፡፡
5.     ዕቅድ ብለው ያስቀመጡት ጉዳይ ዕድሜን ለማራዘም የተጠቀሙበት ዕቅድ ነው፡፡ ብቸና ላይ የመልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬን እና የአለቃ አያሌው ታምሩን መታሰቢያ እንገነባለን ብለዋል፡፡ መልአከ ብርሃንን በተለይ ህዝቡ አያውቅም አሉ፡፡ እኛስ እናውቃቸዋለን በመጽሐፋቸው ተምረናል የማያውቃቸው ቅባቱ ማኅበረሰብ ብቻ ነው፡፡ በግድ አላውቅም ብሎ ማት ነው እንጅ መልስ ስለመለሱላቸው ያውቋቸዋል፡፡ ባሶ ሊበን ላይ ታሪካቸው ተዳፍኖ የቀረ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ የሚባሉ አሉ መታሰቢያ ይሠራላቸዋል፡፡ ሞጣ ላይም ገብረ ሥለሴ አንጋፋው መታሰቢያ ይሠራላቸዋል ብለዋል፡፡ ይህ ሁሉ ዕድሜያቸውን ያራዘሙ ስለመሰላቸው እንጅ የሚሠሩ ሆነው አይደለም፡፡ ቢሠሩ እንኳ የሚሠራቸው ሕዝቡ ነው እንጅ እርሳቸው አይደሉም፡፡
6.     15፡15 ጀምረው አሜሪካ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር እንተዋወቃለን ይላሉ፡፡ 15፡30 ላይ ሰው አባ ከተባለ ያው ነው ጳጳስ ነው ማለታቸው ነው፡፡ ምንኩስና እና ጵጵስናን አንድ ሲያደርጉ ትሰማላችሁ፡፡ አረ ስንቱ ኡፍፍፍፍ!!!
7.     ምሥራቅ ጎጃም ላይ እንዲህ ያለ ህንጻ ይቆማል ብሎ በህልምም የሚስብ የለም ነበር ያሉት 7፡12 ላይ የተናገሯት ነገር በጣም ታሳዝናለች፡፡ ምሥራቅ ጎጃም ከዚህ የበለጠ ህንጻ አልገነባም እንዴ አብማን አታዩም ገዳመ አስቄጥስን አታዩም በጣም ያሳዝናል፡፡ ራስን ሰማይ ለመስቀል ሲሉ ከስር ያለውን ምእመን ሥራ ማበላሸት ደስ አይልም፡፡
እናንተ በሙሉ አዳምጡት፡፡ የምረቃውን መርኃ ግብር በተመለከተ በዚሁ እፈጽማለሁ፡፡ በቀጣይ የአቡነ ማርቆስን በምሥጢር የተቀረጸ መረጃ እለቅላችኋለሁ፡፡ የቅዱስ ማርቆስ ሰንበት ትምህርት ቤትንም አልረሳሁትም፡፡ አቡነ ማርቆስ ጠባቸው ከምእመናን ጋራ ብቻ አይደለም ከዞኑ አስተዳድር ጋራ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋራ ነው ከሁሉም ጋር ነው፡፡
በውስጥ መስመር መረጃዎችን የምትልኩልኝን ሁሉ በፈጣሪ ስም ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ በነገራችን ላይ መረጃ ሳይኖራችሁ በውስጥ መስመር እየመጣችሁ “ሃይ” ስትሉ የምትውሉ ቦዘኔዎች ምንም ዓይነት ምላሽ አትጠብቁ ሥራ ፈት መሰልኳችሁ እንዴ? መረጃ ካላችሁ ብቻ በውስጥ መስመር አግኙኝ ከሌላችሁ አታድርቁኝ፡፡ በርካታ መረጃዎች እየጎረፉልን ነው በቀን በቀን እየተቆጠበ ይለቀቃል፡፡
ዘመነ ማርቆስን ለቤተክርቲያናችን እናድርገው፡፡




አባ እንባቆም ጫኔ VS ምሥራቅ ጎጃም




ዛሬ ጥቅምት 2/2010 ዓ.ም ነው፡፡
==========================
• ጸሎቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡ የጥቅምቱ ሲኖዶስ አንድ መላ እንዲሰጠን ወደ ፈጣሪ እየተማጸንን ነው፡፡
• እነርሱ ለጥፋት 24 ሰዓት እየሠሩ ናቸው እኛ ለድኅነት እንቅልፍ ሊያሸንፈን አይገባውም፡፡
• ብቸኛው ምርጫ ወደ ፈጣሪ መጸለይ እውነት እውነቱን መነጋገር ብቻ ነው፡፡
• ይህ ፖስት ውሸት ነው የምትሉ ሰዎች በመረጃ አስደግፋችሁ ውሸት መሆኑን አሳውቁ ከዚያ ውጭ ዝም ብየ እለፈልፋለሁ ብትሉ እብድ ያሰኛችኋል፡፡

ምስራቅ ጎጃም አስተዳዳሪ ንግግር በሀገረ ስብከቱ ህንጻ ምረቃ ላይ!




ዛሬ ጥቅምት 1/2010 ዓ.ም ነው፡፡
#ጥቅምት_ባተልን_ይኸው!
#ወይ_ያልፍልናል_ወይ_ያልፍብናል!
============================
• በነገራችን ላይ ሁሉም ወደ ጸሎት ግንባር እንዲሰለፍ ጥሪ ተላልፏል፡፡
• ሁሉም ሰው ስለቤተክርስቲያናችን ፈተና በጸሎቱ እንዲተጋ ለዚሁ ሲባልም ከምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ በመላው ዓለም ያለ ክርስቲያን ሁሉ ለጸሎት እንዲቆም ተነግሯል፡፡
• የቻለ ቆሞ ይጸልይ ያልቻለ ገዳማውያኑን ያሳስብ ተብሏል፡፡
ወደ ዛሬው ዘገባችን ስናመራ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ መስገን ምን አሉ የሚለውን እናገኛለን፡፡ አቶ ተመስገን በመጀመሪያ ደረጃ በዚህ ስብሰባ ማን ማን እንደተገኙ እና በቤተክርስቲያኒቱ ምን ኃላፊነት ላይ እንዳሉ ሳይቀር በዝርዝር ነበር የተናገሩት፡፡ የዚህን አጠቃላይ ንግግር በቪዲዮው የተያያዘላችሁ ስለሆነ እርሱን ተመልከቱት፡፡ በእውነት አቶ ተመስገን ወይ በቤተክህነት ያደገ ነው አልያም ደግሞ ሪፖርቱን የጻፉት የእነአባ ማርቆስ ቡድን ነው፡፡ ይህ በሚገባ ለሁሉም ግልጽ ነው፡፡ አቡነ ቶማስ (ትንሹ አባ ማርቆስ) የመንግሥት አካል እንኳ ሲናገር በቤተክህነት የተማረ ሰው እንጅ የመንግሥት ሰራተኛ አይመስልም ብለው ያሞካሹትም ሪፖርቱን አቶ ተመስገን ስላነበበላቸው ነው እንጅ ስለጻፈው አልመሰለኝም፡፡ ለማንኛውም ግን እርሱ በትክክል የጻፈውን አንብቦ ከሆነ አቶ ተመስገንን አጨብጭቡለት በእውነት እንዴት ያለ ገለጻ መሰላችሁ ያደረገው፡፡ አቶ ተመስገን ሲጀምር በስብሰባው የተገኙትን በሚከተለው ቅደም ተከተል ነበር የዘረዘራቸው፡፡ 

ማክሰኞ 10 ኦክቶበር 2017

አቡነ ቶማስ (የባሶ ቅባቴ) vs ምሥራቅ ጎጃም!


ዛሬ መስከረም 30/2010 ዓ.ም ነው፡፡
መስከረም አለቀ ጥቅምት ገባላችሁ!
=========================
መስከረም 27/2010 ዓም አቡነ ማትያስ በአቡነ ማርቆስ (ቅባቴ) ጥሪ ተደርጎላቸው ያለ ቅዱስ ሲኖዶሱ ፈቃድ ትንሹን አባ ማርቆስ (ቅባቴው አቡነ ቶማስ) አስከትለው የመምጣታቸው ምሥጢር ምን እንደሆነ እንደ ጉድ ይተረክላችኋል፡፡ ደግሞ የተያያዘውን ቪዲዮ ተመልከቱት አደራ ያ ካልሆነ ግን ዝም ብለህ አስተያየት እሰጣለሁ እያልክ እንደ እሳት እራት ጥልቅ እንዳትል አደራ አደራ አደራ!
ትንሹ አባ ማርቆስ (የባሶው ቅባቴ አቡነ ቶማስ) ሐምሌ 9/2010 ዓም በውዱስነታቸው ከተሸሙት ሊቃነ ጳጳሳት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ አባ ወልደ ሃና ጸጋው ይባሉ የነበሩቱ የዛሬው አቡነ ቶማስ ባሶ ሊበን ወረዳ የወንበድ ማርያም በምትባል ቦታ ተወልደው እንዳደጉ ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ ከእርሳቸው ጋራ ባህርዳር ፈለገ ግዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ብቻ የተዋወቃችሁ ሰዎች ካላችሁ ይህንን ሳታነቡት አስተያየት ለመስጠት እንደምትሮጡ የታወቀ ነው፡፡ “ጅብ በማያውቀው አገር ሂዶ ቁርበት አንጥፉልኝ” አለ አሉ ክክክክክ፡፡ አባ ወልደ ሃና ጸጋው የዛሬው አቡነ ቶማስ የአዊ ሊቀጳጳስም ባህር ዳር ሂደው ቁርበት ያስነጠፉ ቅባቴ ናቸው፡፡ ባሶ ሊበን ያላችሁ ታግዙኛላችሁ አሁን ከፍተኛ የሆነ መነቃቃት ያለበት ቦታ ነው፡፡ ተዋሕዶ እና ቅባት እየተባለ መከፋፈል ተጀምሯል፡፡ የተዋሕዶ አናብስት የሆኑ የባሶ ልጆች እንደሚሉት ከሆነ ቅባት የሆነን ካህን መስቀል አይሳለሙም የንስሐ አባትም አያደርጉም በዚህም የተነሣ በካህናት ዘንድ ሳይቀር አብሬ አልቀድስም አብሬ አላገለግልም እስከመባባል ድረስ የደረሰ ልዩነት መፈጠሩን ያወሳሉ፡፡ ታዲያ በባሶ ሊበን የሚኖሩ በቅባት እምነት ውስጥ ያሉ ምእመናንን እውነቱን እየተረዱ ወደ ተዋሕዶ እምነታችን እየገቡ ናቸው፡፡ በመኪና እየሞሉ በራሳቸው ኮንትራት መኪና እየያዙ ከምሥራቅ ጎጃም ወጣ እያሉ #ልጅነት እየተቀበሉ ናቸው፡፡ ይህ ጥሩ ጅማሬ ሆኖም ታይቷል፡፡ #ቁይ ላይም እንዲሁ ተመሳሳይ ሥራ እየተሠራ ይገኛል፡፡  አቡነ ቶማስን ያገኘናቸውም የዚህ ጊዜ ነበር፡፡ አባ ወልደ ሃና ጸጋው ተብለው ይጠሩ በነበሩበት በቆሞስነታቸው ጊዜ ባሶ ሊበን ላይ ከቅባት ወደ ተዋሕዶ የሚመለሱ ሰዎች መጠመቅ አለብን ወይስ የለብንም በሚለው ጉዳይ ላይ አሰጥ አገባ በገቡበት ጊዜ አባው በቦታው እንደሄዱ ለምን አንጠይቃቸውም ይላሉ፡፡ ከዚያማ ቀርበው ይጠይቋቸዋል፡፡ አባ አሉ ምእመናኑ “እኛ ከቅባት እምነት ወደ ተዋሕዶ መመለስ ፈልገን ነበር፡፡ ግን በ40 በ80 በፊት ተጠምቀናል፡፡ አሁን ተዋሕዶ ለመሆን ስንፈልግም ተጠመቁ ብለውን ነበር፡፡ ድጋሜ መጠመቅ ያስፈልገናል” ይሏቸዋል፡፡ አባ ሆየ ያኔ ገነፈለባቸው መሰል “የምን ጥምቀት ነው የምን ተዋሕዶ የምን ቅባት ነው፡፡ እምነት ማለት በሥላሴ ማመን እንጅ ቅባት ተዋሕዶ መባባል አይደለም፡፡ ጥምቀትም አያስፈልግም ቅባት ነኝ ተዋሕዶ ነን ማለትም አይገባም” ብለው እርፍ ይላሉ፡፡ ያንጊዜ ልናስጠምቃቸው ጫፍ ላይ ደርሰው የነበሩቱ ሁሉ “ከአባ ወልደ ሃና በላይ ለሀሳር ነው” እያሉ ዕድሉን ሸሽተው ፈረጠጡ እና አረፉት፡፡ አባ ወልደ ሃና ማለት ለካ ቅባቴ ናቸው ብየ ነገሬን የቋጨሁት ያኔ ነበር፡፡ ደግሞ እኮ አያፍሩ #ደብረሊባኖስ መጻሕፍትን ሊማሩ ሄደዋል፡፡ ታዲያ እዚያም ከመምህራን ጋራ በዚሁ በቅባት በተዋሕዶ ጉዳይ ላይ  መግባባት አልቻሉም ነበርና #ባሕርዳር መጥተው ቁጭ አሉላችሁ፡፡ ሞኙ የባህር ዳር ህዝብም የመጽሐፍ ሊ መጡልን እያለ እግራቸው ሥር እየተነጠፈ ቅባቱን ሲቀባ ከረመላችሁ፡፡ ቅባቱ ለምን ባህር ዳር ብቻ ተወስኖ ይቀራል እርሳቸው ጳጳስ ሆነው ዓለምን በሙሉ በቅባት መቀባት አለባቸው ብሎ የወሰነው የእነአባ ማርቆስ ግሩፕ ለጵጵስና መመልምሎ አዊ ላይ ጉብ አረገላችሁ፡፡ #አዊዎች አሁን ላይ እንዴት አይነት ሊቅ ጳጳስ መጣልን እያሉ ናቸው አሉ ድንቄም ሊቅ፡፡ እውቀት አርዮስን ገድሏል እውቀት ግኖስቲካውያን እንዳይነሡ አድርጎ ሲዖል ነው የወረወራቸው፡፡ ከዚያስ አላዋቂ የተባለው አባ ሕርያቆስ ምንኛ ድንቅ ድርሰትን እንደ ደረሰ ልብ በሉ፡፡

ታዲያ ከቁምስና እስከ ጵጵስና ድረስ ከጎናቸው ሳይለዩ በቅባት የተዋወቁትን አባ ማርቆስ ምስራቅ ጎጃምን በቅባታቸው እንዲያባብሱ ከህዝቡ ጋራ በግድ ሊስማሙ ደብረ ማርቆስ ከተማ የመጡት የአዊው አቡነ ቶማስ ቅባቴ ምን አሉ መሰላችሁ “ለቅዱስነታቸው ብዙ ወሬ ይወራላቸው ነበር ዛሬ ግን በዓይናቸው አዩት በጆሯቸው አይደለም የሰሙት ዛሬ ዓይተውታል፡፡ ሰውን የሚገልጠው ሥራው ነው ወሬው አይደለም አለባበሱም አይደለም” ምናምን ምናምን ብለው ሞቱ እንደቀረበው ውሻ ሲያላዝኑብን አልዋሉም መሰላችሁ፡፡ በአጋዚ ጦር ታጅቦ እንዲህ ያለ ድንቅ ቅባታዊ ንግግር ያደረጉት ብጹነታቸው አቡነ ማርቆስ ማለት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት ናቸው ብለው ከጌታ ጋራ እያነጻጸሩ እና እያወዳደሩ ሲያሞጋግሷቸው ውለዋል፡፡ ይችም ውለታ ትሁን አይ አንች እናት ዓለሜ ቤተክርስቲያን፡፡ትንሹን አባ ማርቆስ አቡነ ቶማስ ቅባቴን  ባሶ ሊበን አቀባበል ሲደረግላቸው አቡነ ማርቆስ ትልቁ ቅባቴ ስጦታ ሰብስበውላቸዋል ለካ የዚያንን ውለታ መመለሳቸው ነው፡፡ ምሥራቅ ጎጃም ጥያቄው የእምነት ነው አባ ቶማስ እና ሌሎችም ተናጋሪዎች እምነት የሚሉት ህንጻ መስራትን ነው፡፡ አንድ ሊቀጳጳስ ህንጻ ግንባታን ከምእመናን ድህነት ጋራ አያይዞ ማስተማር ነበረበትን፡፡ በእርሳቸው ቤት የባሶ ተወላጅ ስለሆኑ ብቻ የተናገሩትን ሁሉ አሜን ብሎ የሚቀበል የደብረ ማርቆስ ህዝብ ያለ መስሏቸዋል ወይ ፍንክች አለ፡፡ ሲጀመር በጦር ተከባችሁ መምጣታችሁ አሳፍሮን ስለነበር ከእናንተ ምንም ነገር ፍሬ ያለው ትምህርት አልጠበቅንም ነበር፡፡ እኔስ ደግሞ የሚገርመኝ በዚያ በጋንቤላው ሊቀ ጳጳስ በአባ ሩፋኤል የሚመረው ሲንቦጫረቅ የዋለው ጭብጨባ ነው፡፡ አጨብጫቡ ሁላ ጥቅምት ሲኖዶስ መድረሻህን ያሳጣሃል፡፡ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ቢደረድሩት መፍረሱ አይቀርም በእምነት በምግባር ማነጽ ግን ምንኛ መታደል ነበር፡፡ ነገር ግን ምእመናንን ለማነጽ የሚያበቃ ምግባርም እምነትም የሌላቸው ሰዎች መድረክ ላይ እየወጡ አባ ማርቆስን ተቀበሏቸው እያለ እንደ ቁራ መጮኹ ትንሽ ያሳፍራል አረ በጣም ያሳፍራል የምን ትንሽ ነው፡፡

ለማንኛውም #አዊዎች ዝም ብላችሁ አትበሉ እውነቱን እውነት ብላችሁ አባ ቶማስን ተቃወሙ፡፡ በጥቅምት ሲኖዶስ ምሥራቅ ጎጃምን ሊሰጡ ይችላሉ ብለን እንገምታለን፡፡ ይህንን የምንልበትም ምክንያት አባ ቶማስ የአባ ማርቆስን ራዕይ የሚያስቀጥሉ ትንሹ ቅባቴ ናቸውና ነው፡፡ አዊ ላይ እምነትህን ጠብቅ ብለው ቢያስተምሩህ እምነትህ ተዋሕዶ ስለሆነ እንዴት ያሉ መምህር አገኘን ትል ይሆናል ምሥራቅ ጎጃም ላይ ግን እምነትህን ጠብቅ ማለት ቅባትነትን ወይስ ተዋሕዶነትን ግራ ያጋባሃል፡፡ #አዊዎች እስኪ አቡኑ ሲያስተምሩ ቀርጻችሁ ላኩልኝ፡፡ አንድ ነገር ለ #አዊዎች ልናገር አባ ቶማስ ሲያስተምሩ #ተዋሕዶ ብለው ያውቃሉ ወይ፡፡ እባካችሁ ልብ ብላችሁ አፋቸውን ጠብቃችሁ አዳምጡ፡፡ የሚቀረጸውን ቅረጹ የሚጠየቀውን ጠይቁ፡፡ እርስዎን ቅባት ነዎት እያሉ ሰዎች ይናገራሉ ይህ እውነት ነው ወይ ብላችሁ ጠይቋቸው ይህንንም ከፈራችሁ #ተዋሕዶ እና #ቅባት ልዩነታቸው ምንድን ነው ብላችሁ ጠይቃችሁ መረጃ ያዙ፡፡
አባ ቶማስ በመጨረሻም ለአቡነ ማርቆስ ቅኔ ቢጤ ተቀኝተውላቸዋል፡፡ ክክክክክክ አይ መወዳደስ አይ ከንቱ ውዳሴ መሻት አይይይ አምላክ ፊት ምን እንል ይሆን፡፡ ይህ የሽንገላ ከንፈር ሁሉ ዲዳ የሚሆንበት ዘመን ይመጣል ያኔ የት እንገባ የት እንሸሸግ ይሆን፡፡
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ተመስገንም በጊዜው ሪፖርት አቅርቧል፡፡ አባ ማርቆስም ስላወደሷቸው በሞቅታ ተነሥተው ተናግረዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ሙሉ መረጃ ነው ያ ብቻ እናንተ በትእግሥት ጠብቁኝ፡፡ በነገራችን ላይ የጽጌ ጾም ነበር የምረቃው ጊዜ፡፡ ብዙ ሰንጋዎች እንደታረዱ ሰምተናል መረጃው ያላችሁ ፎቶ ቪዲዮ ያላችሁ ላኩልን በውስጥ መስመር፡፡


ዘመነ ማርቆስን ለቤተክርስቲያናችን ብቻ እናድርገው!!!

ሰኞ 9 ኦክቶበር 2017

አቡነ ማትያስ vs ምሥራቅ ጎጃም

 

ዘሬ መስከረም 29/ 2010 ዓ.ም ነው፡፡
=======================
የምሥራቅ ጎጃም ምእመናን ይበልጥ ውስጣቸው ነዷል፡፡ ችግር ይፈታሉ የተባሉቱ ቅዱሱ ፓትርያርክ ይኸው ላችሁ የአባ ማርቆስን  ተምህርት ተቀበሉ ካልተቀበላችሁ የራሳችሁ ጉዳይ ነው በማለት ሲያቀረሹብን ዋሉ፡፡ ዕለቱ ቅዳሜ ነው ቀኑ 27 መድኃኔዓለም  መስከረም ሊገባደድ 3 ቀናት ብቻ የቀሩበት ዕለት አባ ማትያስ ልጆቻቸው የተባሉትን በሙስና እና በክህደት የተዘፈቁትን ጳጳሳት እና ሥራ አስኪያጆች አስከትለው (የተወሰኑት ግን ነጻ ናቸው)  ህንጻ ሊመርቁ በቦታው ተገኙ፡፡ አቡኑ በአጋዚ ወታደር ታጅበው ወደ ከተማዋ የገቡት በ26 ሰርክ ሰዓት አካባቢ ነበር፡፡ አይ አባ ማትያስ ሌባ እና ከሐዲ አስከትለው ከታላቁ ሐገር ጎጃም እንዲህ ዱብ ይላሉ፡፡ ትዝ አለዎት ያኔ በሚያዝያ 2009 ዓ.ም እርስዎ መፍትሔ ይሰጡናል ብለው የመጡትን ምእመናን ከምንም ሳይቆጥሩ ሲሸኟቸው ዛሬ  እርስዎም የእጅዎን አገኙ፡፡ አንድ ፓትርያርክ በአጋዚ ወታደር ታጅቦ ሲመጣ አቡነ ቴዎፍሎስን በተመለከተበት ዓይኑ የጎጃም ሕዝብ እንዴት እርስዎን ፓትርያርከ ናቸው ብሎ ይቀበልዎ አዩት አይደል፡፡ አንድ ምእመና ሳይገኝ በአጋዚ ወታደር እና በሥርዎ በሸጎጧቸው ከሀድያንና ሙሰኞች ብቻ ታጅበው ወደ ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን አመሩ፡፡
ልጆችዎ የተባሉቱ እነ አቡነ አረጋዊ የደቡብ ጎንደር ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ የሽረ እንዳ ሥላሴው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሩፋኤል የጋንቤላ እና ደቡብ ሱዳን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቶማስ ( የባሶው ቅባቴ) የአዊ ሊቀ ጳጳስ እነ ዘራፊው ሙሰኛው ጎይቶም ያይኑ የአዲስ አበባው ሀገረ ስብከት  እነ መናፍቁ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ አረ አሳቃችሁኝ አባቴ፡፡ የሆነ ግሩፕ መፍጠር ጀመራችሁ ልበል አዎ ፈጥራችኋል እንጅ፡፡ ይህ ሁሉ ዘራፊ እና መናፍቅ ደብረ ማርቆስ መምጣት ለምን አስፈለገው ይህ ህንጻ ይህን ያህል ሽር ጉድ የሚባልለት ግዙፍ ህንጻ እኮ አይደለም ቢሆንም የምእመናን ትጋት እንጅ የአቡነ ቅባት ትጋት እንዳልሆነ ማዎቅ ለምን ተሳናችሁ፡፡
እኛ አቡነ ማርቆስን እንዲነሡልን ስንጠይቅ እኮ እምነታችንን በረዙብን ቅባትን አስፋፉብን ክህደቶችን አስተማሩ ሀብታችንን መዘበሩ ብለን ነው እንጅ ፎቅ አልገነቡልንም ብለን አይደለም፡፡ ፎቁማ ከራሳችን ኪስ በተሰበሰበ ገንዘብ የተገነባ እኮ ነው፡፡ እስኪ የስንት ወር ደመወዛቸውን ለቀዋል ለዚህ ህንጻ ክክክክክክ አረ አታስቀኝ በለኝ ወዳጀ፡፡ እርሳቸው በዚህ ህንጻ ግንባታ ስም ከውጭ አገር ሳይቀር ገንዘብ ሰብስበውበታል ለምነውበታልም እናም የራሳቸውን ህንጻ ቪላ ቤት ግንብተውበታል፡፡ አዲስ አበባ የምትኖሩ ሰዎች ይህንን ቪላ ቤት ታውቁታላችሁ እናንተው ናችሁ የነገራችሁንና፡፡ የአንድ ጳጳስ ሥራ ግን ሕንጻ መገንባት ነው እንዴ? ለዚያ ነው ለካ ለጵጵስና መመልመያ መስፈርቱ ላይ ስለ እምነት እና ምግባር ትኩረት ያልሰጠው፡፡ ተግባባን ወዳጀ አንተ ቤተክርስቲያናትን ካሳነጽክ የንግድ ህንጻዎችን ከገነባህ ነገ ጳጳስ ነህ በቃ ጳጳስ አልኩህ፡፡ የሚገርምህ እኮ መናፍቅ መሆንም ትችላለህ መመዝበርም ትችላለህ ብቻ አንተ ጥሩ ሪፖርት ፀሐፊ መሆን አለብህ፡፡ አይ አንች እናትዓለም ቤተክርስቲያን፡፡
አጠቃላይ የስብሰባው የምረቃው መርኃ ግብር ሂደት ከሞላ ጎደል ከንቱ ውዳሴዎች የሰፈኑበት ህንጻ ህንጻ ሲባል የዋለበት ነበር፡፡ እንደነገርኋችሁ አቡና ማትያስ ሲመጡ አቀባበል ያደረገላቸው የከተማ ሕዝብ የለም ነበር ሰንበት ትምህርት ቤቶችን የሉም ነበር፡፡ እርሳቸው በደረቁ እንደተቀበሏቸው እርሳቸውንም በደረቁ ነው የተቀበሏቸው፡፡ አጋዚው ግን የሆነ ሽብር የተፈጠረ ነበር የሚመስለው አይ አባት በአጋዚ ታጅበው መጡልን እና አረፉት፡፡ በዚህ መካከል መእመናን ቢመጡ እኮ አመፀኛ ተብለው መታሰራቸው መገደላቸው ነበር ማለት ነው እንኳንም ቀርተዋል፡፡
በነገራችን ላይ የከተማዋ መንግሥት (ክክክክክክክ) አቡነ ማትያስ እንደሚመጡ ከሰሙበት ቀን ጀምረው ሕዝቡ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እና ሌሎችን ለእምነታቸው ቀናዒ የሆኑ የከተማው ነዋሪዎች አቡነ ማትያስን በጥያቄ እንዳያዋክቧቸው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ይሰሩ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዚህም መሠረት ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ሰብስበው በአቡነ ማትያስ ፊት ልታደርጉት ያሰባችሁ ሦስት ነገር አለ ይኸውም በፊታቸው ማልቀስ ወረቀት በትናችሁ ቅስቀሳ ማድረግ ወዘተ አስባችኋል እና ከዚህ ሥራችሁ እረፉ ተቆጠቡ ብሎ አስፈራርቷልም ተብሏል፡፡ በዚህም መሠረት አባ ማትያስ ጆሯቸው መስሚያ እንደሌለው የተረዱት የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በአቀባበሉ ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል፡፡ ምእመናን ላይም ተመሳሳይ የሆነ ነገር ተሰርቷል፡፡ ሆኖም ግን በዚህ በአቀባበሉ ወቅት የማንም ተወካይ አለመገኘት መንግሥትንም ስላሳሰበው ቢያንስ ለ27ቱ  ተወካይ ላኩ ብሎ መልእክት በማስተላለፉ ከሰንበት ትምህርት ቤት እና ከምእመናን ጥቂት ጥቂቴ ተወካዮች በቦታው ለመገኘት ችለዋል፡፡ እዚህ ቦታ ለመገኘት ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ለማግኘት እንደሚደረገው ያለ ፍተሸ እና ቁጥጥር ነበር አይ ቅዱስ አባት፡፡ ህዝቡ እና ሰንበት ትምህርት ቤቶች መንግሥት ባደረገላቸው ጥሪ ብቻ ተወካይ የላኩ ቢሆንም በእነ አባ ሩፋኤል ጀማሪነት ሲንቦጫረቅ የዋለውን ጭብጨባ ከመስማት ባለፈ ምንም ሳይተነፍሱ ዕድሉ ተነፍጓቸው ሲበሳጩ ውለው መመለሳቸውን ነግረውናል፡፡ አንዱ ተሳታፊ እንደነገረን ከሆነ “አቀማመጣቸው በራሱ እኛ እንድንናገር ዕድል አልፈጠረልንም” ብለዋል፡፡ አቀማመጡ እንዴት ነበር ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄም ሲመልሱ “መጀመሪያ ቅዱስ ፓትርያርኩ አሉ ከዚያ ጳጳሳት ከዚያም ሥራ አስኪያጆች ከዚያም በተጠንቀቅ የቆመ የአጋዚ ወታደር አለንጋውን ይዞ ከዚያ በኋላ ነው እኛ ምእመናን እና ልጆቻችን የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተቀመጥን” አሉ፡፡ በቤተክህነቱ እና በህዝቡ መካከል መንግሥት ጦሩን አቁሞ አባትን ከልጅ ሲለያይ ተመልከቱልኝማ፡፡ በነገራችን ላይ አባ ማትያስ ወደዚህ የመጡ የህዝቡን አቤቱታ ሊሰሙ ሳይሆን አቡነ ማርቆስን ለማሞካሸት ነው፡፡ በቅዱስ ሲኖዶሱ አጣሩ ተብለው የተወከሉትን አካላት በፈቃዳቸው ያዘገዩ እስካሁንም ድረስ ችግሩን የሚያጣራ አካል አለመምጣቱ ምንም አታመጡም የሚል መልእክት ያለው ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ቤተክርስቲያኒቱ የምትመራው በቅዱስ ሲኖዶስ መሆኑ ቀርቶ በፓትርያርኩ መሆን የጀመረችው በአቡነ ጳውሎስ ዘመን እንደሆነ ሁሉም ያውቀዋል፡፡ አቡነ ማትያስም የአቡነ ጳውሎስን ራዕይ የሚያስፈጽሙ መንግሥት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የጫናቸው ሸክም ሆነዋል፡፡ ደግሞ ሰደባቸው በሉና እምቡር እምቡር በሉ እንጅ መቸስ የእናንተ ጊዜ አይደል፡፡
የምሥራቅ ጎጃም ሕዝብ የአቡነ ማርቆስን ትምህርት መስማት አለበት ብለው እኮ ነው መመሪያ ያስተላለፉ፡፡ ለማንኛውም የጥቅምቱ ሲኖዶስ ያስተዛዝበናል፡፡ አንድ ፓትርያርክ እንዲህ ያለ ጠባብነት ሲሰብክ ማን ይሰማዋል፡፡ ከፓትርያርኩ በላይ ሆነህ አረፍከው በሉኝ ደግሞ፡፡ ሳጥናኤል መልአክ እንደነበረ አውቃለሁ ግን እበልጠዋለሁ በቃ የሚወዳደረው ቆባችን ሳይሆን እምነታችን ነው፡፡ ወይ እኩል እምነት ይኖረን እና በምግባር እንበላለጣለን እንጅ በእምነት የማይመስል ሰው ግን ሲጀመርም ሊወዳደረን አይችልም በጭራሽ፡፡ ሲኖዶሱ ምንም በሉት ምን መንፈስ ቅዱስ ይመራዋልና ሀሰተኛ ሁሉ ልሳኑ ይዘጋል፡፡ አባ ማርቆስ ደጋፊዎቻቸውን ለማስፋት አዳዲስ ጳጳሳትን በተለይ ለመያዝ ሞክረዋል፡፡ የጋንቤላው የደቡብ ጎንደሩ የሽሬው የአዊው እነ ጎይቶም እነ ኤልያስ አብርሃ ናቸው የአባ ማርቆስ ወዳጆችና ደጋፊዎች፡፡ በነገራችን ላይ የሌባ እና የከሀዲ ስብስብ ይዘው መጡ እንዳይባሉ እነ አቡነ መልከጼዴቅን እነ አቡነ ፊልጶስን እነ አቡነ ዲዎናስዮስንም አስከትለዋቸዋል፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን እኛ ሁሉን ነገር ቀድመን አውቀነዋል ሰሚ የለም፡፡ ይህንን ጉባዐየ ጠብቀን የነበረው ከጥቅምቱ ጉዞ ቢያሳርፈን ተብሎ ነበር አሁን ግን ጥቅምት ላይ ያው ከባለፈው በበለጠ ሁኔታ ምሥራቅ ጎጃም አጠቃላይ አዲስ አበባ መግባቱ አይቀርም፡፡
አንድ ነገር ረሳሁ አባታችን! አቡነ ማርቆስን ግን አያውቋቸውም ልበል ስማቸውን ለመጥራት በጣም ሲንቀጠቀጡ ተስተውለዋል እኮ፡፡ ብጹእ አባታችሁ አቡነ ነነነነነነነነነነነነነነነነነ ኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧኧ ሲሉ ውለው ማን ነው አቡነ ማርቆስ ይላሉ ክክክክክክ ዛሬ ተዋወቁ እንጅ ባይሆን፡፡ ግን ሲመስለኝ ሲመስለኝ ቤተክርስቲያኒቷን ለማጥፋት ብዙ ውጥን ሥራ አላችሁ፡፡ ከዚያም አንዱ ይኸው አሁን ያየነው ጉዳይ ነው፡፡ ለማንኛውም የመንግሥትን የአቡነ ቶማስን የአቡነ ማርቆስን ንግግሮች ወደፊት እንደሁኔታው ሳልቆርጥ ሳልቀጥል በሙሉ እልክላችኋለሁ፡፡
·         በነገራችን ላይ በምሥራቅ ጎጃም የተሐድሶ መናፍቅ መስራች የሆነው ይኼነው በዚህ ጉባዔ ተሸልሟል፡፡
·         ከ700 ሺህ ብር በላይ ያበረከተው እና የህንጻውን ዲሳይን ከመስራት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ባለው ክትትል ከፍተኛ ሥራ እየሰራ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን ምንም እንዳልሠራ ተደርጎ ሪፖርት ቀርቧል፡፡
·         ቅባቶች መጽሐፋቸውን በይፋ ለመሸጥ በመቻላቸው በጉንደ ወይን ወረዳ ቤተ ክህነት በኩል  አቡነ ማርቆስን ሸልመዋል፡፡
·         ከ500ሺህ ብር በላይ የጉልበት ድጋፍ ያደረጉ የግቢ ጉባዔ ተማሪዎች በሪፖርቱ  ስማቸው አልተነሳም፡፡
·         በሀገረ ስብከቱ የሚገኙት ቄስ አበበ የተባሉ አገልጋይ በጉልበታቸው ቀን ከሌሊት ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይሉ ሲሰሩ የነበሩ እና ለህንጻው እዚህ ደረጃ መድረስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሆነው ሳለ ስም አጠራራቸው በሪፖርቱ እንዳይካተት ተደርጓል፡፡

ዘመነ ማርቆስን ለቤተክርስቲያናችን ብቻ እናድርገው!

ዓርብ 29 ሴፕቴምበር 2017

የምሥራቅ ጎጃም ምእመናን VS ቤተክህነት ክፍል 2


ዛሬ መስከረም 19/2010 ዓ.ም ነው፡፡
ነሐሴ 25/2009 ዓ.ም የተካሄደውን የምእመናን እና የካህናት የውይይት መድረክ ነው እየጻፍን ያለነው፡፡
በቤተ-ክህነቱ በኩል የተሰጡ መልሶች
1.     የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የሚገኘው የቆጋ ኪዳነ ምህረት ገዳም አሳታሚነት የታተሙት መጻሕፍት የታተሙ በአቡነ ዘካርያስ ዘመን እንጅ በአቡነ ማርቆስ ዘመን አይደለም የሚል አሳፋሪ መልስ ሰጥተዋል፡፡ ይህን አሳፋሪ መልስ የሰጠው ደግሞ ባህረ ጥበብ የተባለው የሀገረ ስብከቱ ትምህርት ክፍል መምሪያ ኃላፊና ባለ ብዙ ወንበሩና ባለ ሦስት ደመወዙ ሰው ነው፡፡  ማብራሪያ ሲሰጥ ደግሞ ምንም እንኳ መጻሕፍቱ በአቡነ ማርቆስ ዘመን ባይጻፉም ሁለቱን መጻሕፍት የሚሸጡትን ሁለቱን ገዳማት ምስካበ ቅዱሳን ቆጋንና በደ/ማርቆስ ወረዳ ቤተ-ክህነት ስር የሚገኘውን አባ አስራት ገዳም ከዚህ ስራቸው እንዲቆጠቡ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ጽፈናል የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡
እዚህ ላይ እስኪ ማብራሪያ እንጨምርበት፡፡

አባ ወልደ ትንሣኤ ባንቲገኝ VS መልእልተ አድባር ቅዱስ ማርቆስ ሰ/ት/ቤት

ዛሬ ጥቅምት 5/2010 ኣ.ም ነው፡፡ ============================= ·          ጸለተ ምሕላው እንደቀጠለ ነው፡፡ ·          ጽጌን በቤተክርስቲያን እያደርን በረከተ ሥጋ ወነ...